loading
ናይጀሪያዊቷ እጩ ተወዳዳሪ ራሳቸወን ከምርጫ አገለሉ::

ናይጀሪያዊቷ እጩ ተወዳዳሪ ራሳቸወን ከምርጫ አገለሉ:: በቦኩ ሀራም የታገቱ ልጃገረዶችን ለማስመለስ በሚያደርጉት ጥረት ስማቸው ጎልቶ የሚታወቀው ኦቢ ኤዚኩሲሊ ከፉክክሩ የወጡት የቡሀሪን መንግስት ለማሸነፍ ለጠንካራ የጥምረት ፓርቲ ድጋፋቸውን ለመስጠት ነው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ኤዚኩሲሊ ፓርቲያቸው አላይድ ኮንግረስ ፓርቲ ኦፍ ናይጀሪያ ኮሊዥን ፎር ቪያብል ኦልተርኔቲቭ  የተባለ ጥምረት እንዲመስርት ነው ቦታቸውን የለቀቁት፡፡ እኔ ራሴን ከተወዳዳሪነት ያገለልኩበት ዋናው ምክንያት ጥምረቱን […]

ሩሲያ ቪንዙዌላ ጣልቃ ገብነቷን እንድታቆም አሜሪካን አስጠነቀቀች::

ሩሲያ ቪንዙዌላ ጣልቃ ገብነቷን እንድታቆም አሜሪካን አስጠነቀቀች:: በኒኮላስ ማዱሮ አስተዳደር የተማረሩ  ቪንዙዌላዊያን ለውጥ እንፈልጋለን በማለት ጎዳና ወጥተው ፍላጎታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡ ይሄን ተከትሎም ከዋሽንግተን ድጋፍ ያገኙት ተቃዋሚው ጁአን ጉዋይዶ እራሳቸውን ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አድርገው መሾማቸውን በአደባባይ ተናግረዋል፡፡ የቬንዙዌላ የቅርብ ወዳጅ የሆነችው ሞስኮ ዋሽንግተን ጣልቃ ገብነቷን ከቀጠለች በውጤቱ ከባድ ጥፋት ይከተላል ብላለች ፡፡ የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር […]

ቅዱስ ጊዮርጊስ ደረጃውን ማሻሻል የቻለበትን ውጤት አስመዝግቧል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሀግብር ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል ።

በክልል ስታዲየም ጅማ ላይ ጅማ አባ ጅፉር ወላይታ ድቻን አስተናግዶ በአስቻለው ግርማ እና ማማዱ ሲዲቤ ጎሎች 2 ለ 0 መርታት ችሏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ በወጣቶች የተገነባውን ደደቢት ገጥሞ በተመሳሳይ 2 ለ 0 አሸንፏል ።

ለፈረሰኞቹ የድል ጎሎቹን በመጀመሪያው አጋማሽ አጥቂው ሳላዲን ሰኢድ በቅጣት ምት በማስቆጠር ቀዳሚ ሲያደርግ፤ በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ ላይ በጌታነህ ከበደ ተቀይሮ የገባው  አቤል ያለው ምርጥ ችፕ አስቆጥሯል።

ጊዮርጊሶች ያገኟቸውን የግብ አጋጣሚዎች ቢጠቀሙ ኑሮ የሚቆጠረው የጎል መጠን ከፍ ባለ ነበር ።

ድሉን ተከትሎ ፈረሰኞቹ አንድ ተስተካካይ ግጥሚያ እየቀራቸው ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ቡና በአንድ ነጥብ አንሰው በ21 ነጥቦች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ደረጃውን ማሻሻል የቻለበትን ውጤት አስመዝግቧል።

በቡና እና ጊዮርጊስ መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ዝቅ ብሏል ።

በነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ እሳት ተቀሰቀሰ

በነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ እሳት ተቀሰቀሰ። በደቡብ ክልል አርባ ምንጭ ዞን የሚገኘው የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ ትናንት ማምሻውን መነሻው ያልታወቀ ሰደድ እሳት መቀስቀሱ ታውቋል። ሰደድ እሳቱ በተለይም የእግዜር ድልድይ የሚሰኙትን ሰንሰለታማ ተራሮች እየተዛመተ ነው ተብሏል። በአካባቢው የሚገኙ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት  በፓርኩ የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት በንፋስ ምክንያት በስፋት በመዛመት ላይ ሲሆን ጉዳቱን ለመቀነስ የመከላከያ ሰራዊት አባላት […]

የአዴፓ አዲስ አርማ ይፋ ሆነ

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አዲሱን አርማውን ትናንት ይፋ አድርጓል ፓርቲው የአርማ ለውጥ ውሳኔውን ያሳለፈው ባለፈው መስከረም ወር ባካሄደው 12ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ እንደነበር ይታወሳል።

አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው የ14 ቀን ቀጠሮ ተሰጣቸው

አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው የ14 ቀን ቀጠሮ ተሰጣቸው፡፡ ጉዳዩ በአዲስ አበባ እንዲታይና ዋስትና እንዲሰጣቸው ያቀረቡት ጥያቄም ውድቅ ሆኗል፡፡ አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ በተጠረጠሩበት የጥረት ኮርፖሬት የሀብት ብክነት ጉዳይ ዛሬ በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩና ጉዳዩ አዲስ አበባ እንዲታይላቸውም ጠይቀዋል፡፡ […]