loading
በምዕራብ ኦሮሚያ ሶስት ዞኖች 18 የመንግስትና የግል ባንኮች ተዘረፉ

በምዕራብ ኦሮሚያ ሶስት ዞኖች 18 የመንግስትና የግል ባንኮች ተዘረፉ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ወለጋ፣ ቄለም እና ሆሮ ጉዱሩ ዞኖች በሚገኙ 18 የመንግስት እና የግል ባንኮች ላይ ዝርፊያ መፈፀሙን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታውቋል። የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ዝርፊያው የተፈጸመው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ቅርንጫፎች እንዲሁም በኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ […]

መንግስት በምእራብ ኦሮሚያ የኦነግ ወታደሮች ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ መሰረተ ቢስ ነው ተባለ

መንግስት በምእራብ ኦሮሚያ የኦነግ ወታደሮች ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ መሰረተ ቢስ ነው ተባለ በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች መንግስት የአየር ጥቃት ፈፅሟል በሚል የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሸን ጉዳዮች ቢሮ ባወጣው መግለጫ፥ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እያደረገ ባለው እንቅስቃሴ ላይ የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝቡን ለማደናገር […]

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዋ የሚፈጸሙ የጦር መሳሪያና ህገወጥ ገንዘብ ዝውውር ላይ ባካሄደው አሰሳ ከፍተኛ ውጤት ማግኘቱን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዋ የሚፈጸሙ የጦር መሳሪያና ህገወጥ ገንዘብ ዝውውር ላይ ባካሄደው አሰሳ ከፍተኛ ውጤት ማግኘቱን አስታወቀ።  ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ከ2ሺ በላይ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እና ከ50 ሺ በላይ ጥይቶች ተይዘዋል ብሏል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኢትዮጵያ እና የውጭ ሃገራት ገንዘቦች መያዙንም አስታውቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኢንዶክትሪኔሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው […]

በአማራና ትግራይ ህዝቦች መካከል ግጭትም ይሁን የግጭት ፍላጎትም  የለም አሉ የሁለቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች

በአማራና ትግራይ ህዝቦች መካከል ግጭትም ይሁን የግጭት ፍላጎትም  የለም አሉ የሁለቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ። ርዕሳነ መስተዳደሮቹ ይህንን ያሉት የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች በተለያዩ አከባቢዎች ሲያደርጉት በነበረውን የሰላም ጉዞ ማጠቃለያ መድረክ ላይ ተገኝተው ነው፡፡ በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በጋራ […]

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በቤቶች ልማት ዘርፍ ላይ ከሚሳተፉ የስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች ጋር ተወያዩ

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በቤቶች ልማት ዘርፍ ላይ ከሚሳተፉ የስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች ጋር ተወያዩ የአዲስ አበባ  ከተማ ምክትል ከንቲባ  ኢንጂነር ታከለ ኡማ በቤቶች ልማት ዘርፍ ላይ ከሚሳተፉ የስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች ጋር ተወያዩ። ምክትል ከንቲባው በቤቶች ልማት ላይ ተሳታፊ ከሆኑ የስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች ጋር በያዝነው በጀት ዓመት በሚተላለፉ 134 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች ዙሪያ […]

የአልሸባብ ታጣቂዎች ናይሮቢ ወስጥ ባደረሱት ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ 

የአልሸባብ ታጣቂዎች ናይሮቢ ወስጥ ባደረሱት ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ   ከሟቾቹ መካከል  የአሜሪካ እና የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች እንደሚገኙበት  የሁለቱ  ሀገራት መንግስታት ይፋ አድርገዋል፡፡ የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ጆሴፍ ቦይኔት እንዳሉት ታጣቂዎቹ በአንድ ዘመናዊ ሆቴል ላይ ፍንዳታ በማድረስ እና ተኩስ በመክፈት ነው ጥቃቱን የጀመሩት፡፡ ዘ ኢንዲፔንደንት እንደዘገበው አልሸባብ ለጥቃቱ ሐላፊነት ከመውሰዱም በላይ ደጋፊዎቹ በማህበራዊ  ሚዲያዎች ላይ የደስታ […]

የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ ዋሽንግተን ሊያቀኑ ነው

የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ ዋሽንግተን ሊያቀኑ ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ እና የሰሜን ኮሪያው አቻቸው ኪም ዮንግ ኮል ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው ወደ ዋሽንግተን ከሚጓዙት የፒዮንግያንግ  ባለስልጣናት መካከል ከአሜሪካ ጋር የኮሪያን ልሳነ ምድር ከኒውክሌር ስጋት ነፃ ለማድረግ የሚደራደሩት ይገኙበታል፡፡ የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማቶች በዚህ መልክ ተገናኝተው መነጋገራቸው ኪም እና ትራምፕ በቀጣዩ ጊዜ […]

የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይትና ድርድር የሚመራበት ረቂቅ ደንብ ፀደቀ

የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይትና ድርድር የሚመራበት ረቂቅ ደንብ ፀደቀ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ጋር በቀጣይ የሚያደርጉት ውይይትና ድርድር የሚመራበት 16 አንቀጽ ያለው ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይተው ማፅደቃቸውን፣ በውይይቱ ከተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለማወቅ መቻሉን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ ፓርቲዎቹ ከዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት በጉዳዩ ላይ በጋራ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው፡፡ በውይይቱ […]

ኢትዮጵያና ቱርክ በባህልና በቅርስ ጥበቃ ዘርፍ በትብብር እንደሚሰሩ ተገለጸ

ኢትዮጵያና ቱርክ በባህልና በቅርስ ጥበቃ ዘርፍ በትብብር እንደሚሰሩ ተገለጸ ይህ የተባለው በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳሁን የተመራ የልዑካን ቡድን ከቱርክ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ፕሬዝዳንት ሰርዳር ካም ጋር አንካራ ላይ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡ ሁለቱ አገራት በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ትብብራቸውን ይበልጥ በማጠናከር ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። በዚህ ወቅት ዶ/ር ሂሩት የቱርክ የትብብር ኤጀንሲ በኢትዮጵያ […]