loading
ፒ.ኤስ.ጂ ከፈረንሳይ ሊግ ዋንጫ ተሰናበተ

ፒ.ኤስ.ጂ ከፈረንሳይ ሊግ ዋንጫ ተሰናበተ ፒ.ኤስ.ጂ ባለፉት አምስት አመታት የፈረንሳይ ሊግ ዋንጫን ማንሳት ችሏል፤ ከዚህ ውድድር የማይነቃነቅ የሚመስለው የፓሪሱ ቡድን በሜዳው ፓርክ ደ ፕሪንስ 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡ በዘንድሮው የውድድር ዓመት እስካሁን በሊግ አንድ ሽንፈት አስተናግዶ የማያውቀው ፒ.ኤስ.ጂ መራራ ሽንፈት የተጎነጨው ደግሞ በሊጉ ወራጅ ቀጠና ውስጥ በሚገኘው ገንጎ ነው፡፡ ገንጎን ወደ ግማሽ ፍፃሜ ያሻገሩ ጎሎችን […]

በኮፓ ዴል ሬይ ባርሴሎና ሽንፈት ገጥሞታል

በኮፓ ዴል ሬይ ባርሴሎና ሽንፈት ገጥሞታል በስፔን ኮፓ ዴል ሬይ የመጨረሻ 16ቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ባርሴሎና ከሜዳው ውጭ በሌቫንቴ የ2 ለ 1 ሽንፈት አስተናግዶ ተመልሷል፡፡ ኢሪክ ካባኮ እና ቦርያ ማዮራል ለሌቫንቴ በመጀመሪያው አጋማሽ 20 ደቂቃ ውስጥ ያስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች አሸናፊ እንዲሆን አግዘዋል፡፡ ብራዚላዊው አማካይ ፊልፔ ኮቲንሆ በ85ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት የፍፁም ቅጣት ምት ግብ የቡድኑን ከባዶ መሸነፍ […]

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴራሊዮን አቀኑ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴራሊዮን አቀኑ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሴራሊዮን ጉብኝታቸውን የሚያደርጉት ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ነው። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱን የሚያካሂዱት ከሴራሊዮን ፕሬዚዳንት ጁልየስ ማዳቢዩ በተደረገላቸው ግብዣ መሰረት ነው ተብሏል። በጉብኝቱ ወቅት ሁለቱ ባለስልጣናት የሴራሊዮን እና ኢትዮጵያን ወዳጅነት […]

በአለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በሙሉ ወደአዲስ አበባ ተጠሩ

በአለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በሙሉ ወደአዲስ አበባ ተጠሩ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሁሉም የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ጥሪ ማድረጉን አስታወቀ። ከሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት እንደተገኘው መረጃ ለአምባሳደሮቹ ጥሪ የተደረገው በተለያዩ ወቅታዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይ ገለፃ ለማድረግ ተብሎ ነው። አምባሳደሮቹ ወደአዲስ አበባ የሚመጡት በቀጣዩ ሳምንት ነው ተብሏል።

በአቶ ገላሳ ዲልቦ የሚመራው የሽግግር ኦነግ አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ጋር ተወያዩ

በአቶ ገላሳ ዲልቦ የሚመራው የሽግግር ኦነግ አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ጋር ተወያዩ በአቶ ገላሳ ዲልቦ የሚመራው የኦነግ የአመራር ቡድን መንግስት ያደረገለትን ጥሪ ተከትሎ ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ሀገር ቤት ከተመለሰ በኋላ ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኝቶ ተወያይቷል። በርዕሰመስተዳድሩ ጽህፈት ቤት በተካሄደው የሁለቱ አካላት ውይይት የኦነግ አመራሮች […]

ገንዳውኃ አካባቢ በመከላከያ አባላት ደረሰ የተባለውን ጉዳት የሚያጣራ ቡድን  በአስቸኳይ እንደሚላክ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስታውቀዋል

ገንዳውኃ አካባቢ በመከላከያ አባላት ደረሰ የተባለውን ጉዳት የሚያጣራ ቡድን  በአስቸኳይ እንደሚላክ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስታውቀዋል።   ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ገዱ በምዕራብ ጎንደር ዞን የተከሰተውን ችግር አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ማጣራቱ የሚካሄደው ከፌዴራልና ከሚመለከታቸው አካላት በተውጣጣ ቡድን ነው ብለዋል። እንደ ርዕሰመስተዳድሩ አንድ የኮንስትራክሽን ድርጅት መኪኖቹን ከአንደኛው ፕሮጀክት ወደ ሌላኛው ፕሮጀክት ለማንቀሳቀስ በሞከረበት ወቅት […]