loading
ናይጀሪያዊቷ እጩ ተወዳዳሪ ራሳቸወን ከምርጫ አገለሉ::

ናይጀሪያዊቷ እጩ ተወዳዳሪ ራሳቸወን ከምርጫ አገለሉ:: በቦኩ ሀራም የታገቱ ልጃገረዶችን ለማስመለስ በሚያደርጉት ጥረት ስማቸው ጎልቶ የሚታወቀው ኦቢ ኤዚኩሲሊ ከፉክክሩ የወጡት የቡሀሪን መንግስት ለማሸነፍ ለጠንካራ የጥምረት ፓርቲ ድጋፋቸውን ለመስጠት ነው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ኤዚኩሲሊ ፓርቲያቸው አላይድ ኮንግረስ ፓርቲ ኦፍ ናይጀሪያ ኮሊዥን ፎር ቪያብል ኦልተርኔቲቭ  የተባለ ጥምረት እንዲመስርት ነው ቦታቸውን የለቀቁት፡፡ እኔ ራሴን ከተወዳዳሪነት ያገለልኩበት ዋናው ምክንያት ጥምረቱን […]

ሩሲያ ቪንዙዌላ ጣልቃ ገብነቷን እንድታቆም አሜሪካን አስጠነቀቀች::

ሩሲያ ቪንዙዌላ ጣልቃ ገብነቷን እንድታቆም አሜሪካን አስጠነቀቀች:: በኒኮላስ ማዱሮ አስተዳደር የተማረሩ  ቪንዙዌላዊያን ለውጥ እንፈልጋለን በማለት ጎዳና ወጥተው ፍላጎታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡ ይሄን ተከትሎም ከዋሽንግተን ድጋፍ ያገኙት ተቃዋሚው ጁአን ጉዋይዶ እራሳቸውን ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አድርገው መሾማቸውን በአደባባይ ተናግረዋል፡፡ የቬንዙዌላ የቅርብ ወዳጅ የሆነችው ሞስኮ ዋሽንግተን ጣልቃ ገብነቷን ከቀጠለች በውጤቱ ከባድ ጥፋት ይከተላል ብላለች ፡፡ የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር […]

ቅዱስ ጊዮርጊስ ደረጃውን ማሻሻል የቻለበትን ውጤት አስመዝግቧል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሀግብር ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል ።

በክልል ስታዲየም ጅማ ላይ ጅማ አባ ጅፉር ወላይታ ድቻን አስተናግዶ በአስቻለው ግርማ እና ማማዱ ሲዲቤ ጎሎች 2 ለ 0 መርታት ችሏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ በወጣቶች የተገነባውን ደደቢት ገጥሞ በተመሳሳይ 2 ለ 0 አሸንፏል ።

ለፈረሰኞቹ የድል ጎሎቹን በመጀመሪያው አጋማሽ አጥቂው ሳላዲን ሰኢድ በቅጣት ምት በማስቆጠር ቀዳሚ ሲያደርግ፤ በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ ላይ በጌታነህ ከበደ ተቀይሮ የገባው  አቤል ያለው ምርጥ ችፕ አስቆጥሯል።

ጊዮርጊሶች ያገኟቸውን የግብ አጋጣሚዎች ቢጠቀሙ ኑሮ የሚቆጠረው የጎል መጠን ከፍ ባለ ነበር ።

ድሉን ተከትሎ ፈረሰኞቹ አንድ ተስተካካይ ግጥሚያ እየቀራቸው ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ቡና በአንድ ነጥብ አንሰው በ21 ነጥቦች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ደረጃውን ማሻሻል የቻለበትን ውጤት አስመዝግቧል።

በቡና እና ጊዮርጊስ መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ዝቅ ብሏል ።