loading
በካርቱም የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ አልደገፉም የተባሉ አንድ የሃይማኖት አባት ከመስጊድ ተባረሩ

በካርቱም አንድ የሀይማኖት አባት በሀገሪቱ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ባለመደገፋቸው ህዝቡ ከመስጊድ አባርሯቸዋል ተባለ ። ሱዳን ውስጥ ካሉ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀይማኖታዊ መሪዎች አንዱ የሆኑት ኢማም አብዱል ሀይ ዩሱፍ  ተቃውሟውን  እየመሩ አይደለም በሚል ከአማኞች በቀረበባቸው  ውንጀላ  ነው ከመስጊድ  የተባረሩት። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በተለቀቀ ተንቀሳቃሽ ምስል፤ መንግሥትን በመደገፍ የሚታወቁትን  እኚህን ኢማም አንድ ግለሰብ ሲቆጣቸው ታይቷል። ሮይተርስ እንደዘገበው ባለፈው አርብ […]

የኖቤል ተሸላሚው ሳይንቲስት በዘረኛ ንግግራቸው ማዕረጋቸውን ተቀሙ

የኖቤል ተሸላሚው ሳይንቲስት በዘረኛ ንግግራቸው ማዕረጋቸውን ተቀሙ አሜሪካዊው ሳይንቲስት ዶክተር ጄምስ ዋትሰን በአንድ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ ዘረኛ ንግግር ካደረጉ በኋላ  ማዕረጋቸውን ተነጥቀዋል። በዘረ መል ምህንድስና ምርምር የሚታወቁት የኖቤል ተሸላሚው ሳይንቲስት የጥቁሮችና የነጮች ዐዕምሮ ምጥቀት በዘረ መላቸው ይወሰናል የሚል ዘረኛ ንግግር አድርገዋል። ሳይንቲስቱ እንደ አውሮፓውያኑ  አቆጣጠር በ2007 ተመሳሳይ ዘረኛ አስተያየት ሰንዝረው ይቅርታ ጠይቀው ነበር።

ባለሀብቶች የግብርና ምርቶችን የሚሰበስብ የሰው ኃይል አጣን አሉ፣ ምክንያቱ ደግሞ የፀጥታ ችግር ነው ብለዋል።

ሰፋፊ እርሻዎች ባሉባቸው አካባቢዎች በየጊዜው እያጋጠመ ያለው የፀጥታ መደፍረስ በፈጠረው ሥጋት፣ ባለሀብቶች የግብርና ምርቶችን የሚሰበስብ የሰው ኃይል ማግኘት አልቻልንም እያሉ ነው፡፡ በተለይ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በጋምቤላና በአፋር ክልሎች ምርት መሰብሰብ በነበረበት ጊዜ እያጋጠመ ያለው ግጭት፣ የሰው ኃይል ወደ ሥፍራው እንዳይንቀሳቀስ አድርጓል  ነው ያሉት ባለሀብቶቹ፡፡ የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የጥጥ ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ […]

የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች ለዘላቂ ሰላምና ሃገር ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች ለዘላቂ ሰላምና ሃገር ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ። ከመላው ሃገሪቱ የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች የተሳተፉበት ሃገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል ፡፡ በኮንፈረንሱ ላይ ለወጣቱ ትውልድ ሃገራዊ እሴቶችን በማውረስ ዘመናዊነትን በጥበብ እና በብልሃት እንዲላበስ፥ የሃገር ሽማግሌዎች ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል አሳስበዋል። ሚኒስትሯ የሃገር ሽማግሌዎች ሰላምን ከማስፈንና […]

ጠቅላይ ሚነስትር አብይ አሕመድ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማቡዛን ተቀብለው አነጋገሩ።

ጠቅላይ ሚነስትር አብይ አሕመድ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማቡዛን ተቀብለው አነጋገሩ። ጠቅላይ ሚነስትር አብይ አሕመድ ዛሬ በጽ/ቤታቸው የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማቡዛን ተቀብለው ማነጋገራቸው ተሰምቷል። በህዳር ወር ኢትዮጵያን የጎበኙት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፖሳ ጋር የተደረገው ውይይት ቀጣይ የሆነው የዛሬው ውይይት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነትና ትብብር በማጥናከር ላይ ያተኮረ እንደነበር ከጠቅላይ […]