loading
ቻይና እኛም ቤት ሚሳኤል አለ የሚል መልእክት ለአሜሪካ አስተላልፋለች

  ቻይና እኛም ቤት ሚሳኤል አለ የሚል መልእክት ለአሜሪካ አስተላልፋለች አሜሪካ የቅኝት ነፃነት በሚል ሰበብ በደቡባዊ ቻይና ባህር የምታደርገው የቅኝት እንቅስቃሴ ያሰጋት ቤጂንግ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ለማሰማራት መወሰኗን ይፋ  አድርጋለች፡፡ ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው ቻይና አሰማራቸዋለሁ ያለቻቸው ዲ ኤፍ 26 የተባሉት ሚሳኤሎች እስከ 5 ሺህ 471 ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው ተፈላጊው ኢላማ መምታት የሚችሉ ናቸው፡፡ የቻይናው የውጭ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ ከተለያዩ ሀገራት የተጠሩ 60 የኢትዮጵያ አምባሳደሮችን ሊያወያዩ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ ከተለያዩ ሀገራት የተጠሩ 60 የኢትዮጵያ አምባሳደሮችን ሊያወያዩ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ውይይቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስለተደረገው ሪፎርም ፣ ባለፉት 10 ወራት በተገኙ የዲፕሎማሲ ውጤቶች እና ቀጣይ የውጭ ጉዳይ ተልዕኮ ላይ የሚያተኩር እንደሆነ ተነግሯል፡፡ በተጨማሪም አሁን ካለው ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ ጋር የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ይበልጥ ማስጠበቅ በሚቻልበት ሁኔታ ፣ከዳያስፖራው […]

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ሊያካሂድ ነው

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ሊያካሂድ ነው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከመጭው ሰኞ ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን እንደሚያካሂድ ገለጸ፡፡ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በስብሰባው በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈጻጸም ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ከአፈጻጸም ግምገማ በተጫማሪም በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ እና የለውጥ እንቅስቃሴ ሂደት ላይ ይመክራልም ተብሏል፡፡ እንዲሁም የድርጅት እና የመንግስት የስራ አፈጻጸም ጉዳዮች ላይ […]

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ 147 ጠበቆች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ወሰደ 

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ 147 ጠበቆች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ወሰደ  በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የጠበቆች አስተዳደር እና የነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ደምሴ እንደገለጹት  በ2011ዓ.ም ስድስት ወራት ውስጥ 147 ጠበቆች የስነስርዓት እርምጃ ተወስዶባቸዋል። እንደ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ገለፃ የተቀጡት ጠበቆች በስነ ምግባር ችግር ፣ፈቃድ በወቅቱ ባለማሳደስ እና በስነ ምግባር ችግር ጥፋተኛ የተባሉ ናቸው።  

ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ለሩሲያ የጦር ሰፈር ልትፈቅድ ነው

ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ለሩሲያ የጦር ሰፈር ልትፈቅድ ነው የማዕከላዊ አፍሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሜሪ ኖኤል ኮዬራ ሩሲያ በሀገራችን  የጦር ሰፈር ለመገንባት ያቀረበችውን ጥያቄ በመልካም ጎኑ ነው የምናየው ብለዋል፡፡ ፕሬስ ቴሌቭዥን እንደዘገበው ሩሲያ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወታደሮችን ለማሰልጠን ሙያተኞቿን ስትልክ በመርህ ደረጃ በሀገሪቱ የጦር ሰፈር ለመገንባት የሚያስችላትን ስምምነት አድርጋለች ፡፡ እስካሁን ዝርዝር ሁኔታዎች ላይ ባንወያይም ወደፊት የሁለቱም […]

ፖምፒዮ የኢራንን ተፅዕኖ መቀነስ የሚያስችል ተልእኮ ይዘው መካከለኛው ምስራቅን እየጎበኙ ነው

ፖምፒዮ የኢራንን ተፅዕኖ መቀነስ የሚያስችል ተልእኮ ይዘው መካከለኛው ምስራቅን እየጎበኙ ነው፡፡   የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ኢራን በመካለኛው ምስራቅ መረጋጋት እንዳይኖር ለፈፀመችው ተግባር ተጠያቂ ያደረጉት የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባን ነው፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ ኦባማ በቀጠናው ላለው አለመረጋጋት የኢራንን ሚና ቀላል  አድርገው መመልከታቸው ነው፡፡ ጉብኝታቸውን በዮርዳኖስ የጀመሩት ፖምፒዮ  በቀጣዩ ጉዟቸው ወደ ግብፅ ነው ያቀኑት፡፡   ካይሮ […]