loading
የትግራይ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ህዝቡ በመከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ ሊረበሽ አይገባም አሉ

የትግራይ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ህዝቡ በመከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ ሊረበሽ አይገባም አሉ ህገመንግስቱ እንዲከበርለት የሚጠይቅ ህዝብ ራሱ ህግን በማክበር ቅድሚያ መውሰድ ይኖርበታል ብለዋል ም/ርዕሰ መስተዳድሩ ዶክተር ደብረጽዮን ከኢትዮ ኤርትራ ድንበር አካባቢ ለመልቀቅ ከባድ መሳሪያዎችን ጭኖ የተንቀሳቀሰው የመከላከያ ሰራዊት ኮንቮይ እንቅስቃሴ በሽሬ አካባቢ በገጠመው የነዋሪዎች ተቃውሞ መስተጓጎሉን አስመልክተው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የሰራዊቱ እንቅስቃሴ ህጋዊ ነው ብለዋል። ስለሆነም […]

የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች የሰላም ሳምንት አወጁ

የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች የሰላም ሳምንት አወጁ የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች እስከመጪው እሁድ ጥር 5 ቀን  2011 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የሰላም ሳምንት ማወጃቸው ተነግሯል። በዚህ የሰላም ሳምንት ወቅትም የሰላም እና የመቻቻል የውይይት መድረኮችን ጨምሮ  የተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚካሄዱ መሆኑንም ነው ያስታወቁት። በኢትዮጵያ መረጋጋት እና ዘላቂነት ያለው ሰላም እንዲሰፈን የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም ነው የጉጂ ኦሮሞ […]

መከላከያ ሰራዊት ጎሳን መሰረት ያደረገ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች በፍጥነት በመግባት ኅብረተሰቡን እያረጋጋሁ ነው አለ

መከላከያ ሰራዊት ጎሳን መሰረት ያደረገ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች በፍጥነት በመግባት ኅብረተሰቡን እያረጋጋሁ ነው አለ። መከላከያ ሚኒስቴር ይህንን የተናገረው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የሚኒስቴሩን የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ነው። የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሐመድ እንዳሉት፤ የመከላከያ ሰራዊትን ብቁና ገለልተኛ ለማድረግ ባለፉት 6 ወራት የአሰራርና የአደረጃጀት […]

ሃገር አቀፍ የመጠጥ ውኃ፣ ሳኒቴሽንና ንጽህና አጠባበቅ ተቋማት ቆጠራ እየተካሄደ ነው

ሃገር አቀፍ የመጠጥ ውኃ፣ ሳኒቴሽንና ንጽህና አጠባበቅ ተቋማት ቆጠራ እየተካሄደ ነው ቆጠራው የውሃ ተቋማትን ሁለንተናዊ ይዞታ ለማወቅ የሚያግዝና አገልግሎት የማይሰጡ የውሃ ተቋማትን በፍጥነት በመጠገን ችግሮቻቸውን ለመፍታት የሚያግዝ ነው ተብሏል። የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ እንዳመለከተው ቆጠራው የሚካሄደው ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን በሚቀጥሉት 15 ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል። ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እንደተናገሩት የተቋማት ቆጠራ የተጀመረው […]

በማዳጋስካር ምርጫ አንድሪ ራጆሊና ድል ቀንቷቸዋል

በማዳጋስካር ምርጫ አንድሪ ራጆሊና ድል ቀንቷቸዋል አሸናፊና ተሸናፊዎቹ ፕሬዝዳንቶች እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2009 በሚገባ ይተዋወቃሉ፡፡ የአሁኑን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማሸነፍ ያቃታቸው ማርክ ራቫሎማናና ማዳጋስካርን በፕሬዝዳንትነት ይመሩ በነበረበት ወቅት የአሁኑ ባለድል አንድሪ ራጆሊና ደግሞ የአንታናናሪቮ ከንቲባ ነበሩ፡፡ የኋላ ኋላ ግን ራጆሊና ከመከላከያ ሀይሉ ጋር በማበር ራቫሎማናና ከስልጠን እንዲወርዱ የአንበሳውን ድርሻ ተወጥተዋል ነው የሚባለው ፡፡ ከዚያም ራጆሊና በፈረንጆቹ […]

ሂትሮው አየርመንገድ በድሮን ምክንያት በረራ አቋርጦ ነበር

ሂትሮው አየርመንገድ በድሮን ምክንያት በረራ አቋርጦ ነበር በምእራብ ለንደን በሚገኘው የሂትሮው አየር መንገድ አቅራቢያ ድሮን በመታየቱ  ለሰዓታት በረራ እንዲቋረጥ እና መንገደኞች ባሉበት እዲቆዩ ተደርጎ ነበር፡፡ የአየር መነገዱ ቃል አቀባይ  ከፖሊስ እና ከደህንነት አካላት ጋር  ሁኔታውን እያጠኑት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው መንገደኞቹ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ምክንያት ከበረራቸው እንዲዘገዩ ሲነገራቸው የመደናገጥ ስሜት ተፈጥሮባቸው ነበር ፡፡ በወቅቱ በረራው […]

ሃገር በቀል ዕውቀቶች በምርምር አልፈውና በቴክኖሎጂ ተደግፈው ወደ ህብረተሰቡ ለማውረድ የሚያስችል መመርያ ፀደቀ

ሃገር በቀል እውቀቶች በምርምር አልፈውና በቴክኖሎጂ ተደግፈው ወደ ህብረተሰቡ ለማውረድ የሚያስችል መመርያ ማፅደቁን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር አስታወቀ። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመማር መስተማር ስራዎቻቸው በተጨማሪ የአካባቢያቸውን ማህበረሰብ እና ከዛም አልፎ ሀገሪቱን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ግኝቶችን በምርምር ማምጣት ይጠበቅባቸዋል። በሀገሪቱ የሚገኙ አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎችም በተወሰነ ደረጃ ይህን አብይ ጉዳይ ለማሟላት ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ይታወቃል። ይሁን እንጂ አብዛኞቹ ዪኒቨርስቲዎች […]

የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድከር በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን ጀመሩ

የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድከር በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን ጀመሩ አየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊኦ ቫራድካርን  በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ  አዲስ አበባ የገቡት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ግብዣ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ማርቆስ ተክሌ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድከር በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ […]