በማሊ የተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በአንጻራዊነት ሰላማዊ ነበር ተባለ፡፡
ምርጫው በወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት በኢብራሂም ቡበከር ኬታ እና በተቃዋሚው ሶውማሊያ ሲሴ መካከል ብርቱ ፉክክር ተካሂዶበታል ነው የተባለው፡፡ ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው ሀገሪቱን እየመሩ ያሉት ኬታ ለሁለተኛ ጊዜ የማሸነፍ ዕድል እንዳላቸው እየተነገረላቸው ነው፡፡ በተፎካካሪነት እጩ ሆነው የቀረቡት ሲሴ በበኩላቸው ምርጫውን እንደሚያሸንፉ በልበ ሙሉነት ተናግረዋል፡፡ ሲሴ አያይዘውም ገዥው ፓርቲ የምርጫ ኮሮጆዎችን የራሱ ለማድረግ ሞክሯል የሚል ክስ ማቅረባቸው ተሰምቷል፡፡ […]