loading
አቶ ጀዋር መሀመድ በሻሸመኔ የተፈጸመዉን ድርጊት አወገዘ፡፡

በሻሸመኔ ከተማ ለሰዉ ህይወት መጥፋትና የአካል መጉደል ምክንያት የሆኑ ግለሰቦች ለህግ እንዲቀርቡም በፌስቡክ ገጹ ጠይቋል፡፡ አቶ ጀዋር የሻሸመኔ ህዝብ በታላቅ አክብሮትና ፍቅር ተቀብሎናል፤ነገርግን በከተማዋ ሊቀበለን የወጣዉ ህዝብ ቁጥር ከተጠበቀዉ በላይ በመሆኑና በህዝቡም መካከል ሀሰተኛ መረጃ በመሰራጨቱ ምክንያት የሰዎች ህይወት አልፏል፤ አካል ጉዳትም ደርስዋል ፤ በዚህም በጣም ማዘኑን ተናግሯል፡፡ ተጨባጭ ባልሆነ መረጃ ንጹህ የሆነ ሰዉን መጉዳት […]

በማሊ የተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በአንጻራዊነት ሰላማዊ ነበር ተባለ፡፡

ምርጫው በወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት በኢብራሂም ቡበከር ኬታ እና በተቃዋሚው ሶውማሊያ ሲሴ መካከል ብርቱ ፉክክር ተካሂዶበታል ነው የተባለው፡፡ ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው ሀገሪቱን እየመሩ ያሉት ኬታ ለሁለተኛ ጊዜ የማሸነፍ ዕድል እንዳላቸው እየተነገረላቸው ነው፡፡ በተፎካካሪነት እጩ ሆነው የቀረቡት ሲሴ በበኩላቸው ምርጫውን እንደሚያሸንፉ በልበ ሙሉነት ተናግረዋል፡፡ ሲሴ አያይዘውም ገዥው ፓርቲ የምርጫ ኮሮጆዎችን የራሱ ለማድረግ ሞክሯል የሚል ክስ ማቅረባቸው ተሰምቷል፡፡ […]

የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳላህና የፕሬዚዳንቱ አማካሪ የማነ ገብረአብ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሞቃዲሾ መግባታቸዉን ኤርትሪያን ፕሬስ ዘግቧል፡፡

የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳላህና የፕሬዚዳንቱ አማካሪ የማነ ገብረአብ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሞቃዲሾ መግባታቸዉን ኤርትሪያን ፕሬስ ዘግቧል፡፡ በዛሬው ዕለት ወደ ሞቃዲሾ ያቀናው በውጭ ጉዳዩ ሚኒስትሩ የተመራው ልዑክ በሁለትዮሽ እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የተመራው ልዑክ ወደ ሞቃዲሾ ከማቅናቱ በፊት በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ቆይታ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ግብጽ አምስት ሰዎችን በእድሜ ልክ እስራት ቀጣች፡፡

የግብጽ ፍርድ ቤት የቀድሞውን የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ መሪ ሞሀመድ ባዲን ጨምሮ አምስት ሰዎች በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል ተብሏል፡፡ አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው አሁን ከአራት አጋሮቻቸው ጋር የእድሜ ልክ እስር የተፈረደባቸው ባዲ በ2013 ከተያዙ በኋላ በተናጠል ፍርድ ቤት ቀርበው የሞት ቅጣት ተወስኖባቸው ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ የቀድሞውን የአቅርቦት ሚኒስትር ባሰም ኡዳን በ15 ዓመት እንዲሁም ሌሎች 3 […]

በሚቀጥሉት ሳምንታት በትንሽ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) መድሃኒት የማድረስ ስራ ይጀመራል፡፡

መድሃኒት የማድረስ ስራው ሳይንስ እና ቴክኖሎጄ ሚኒስቴር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እንደሚሰሩት የሳይንስና ቴክኖሎጄ ሚኒስቴር በድረ ገፁ ላይ አስፍሯል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀጣይ አመት በትምህርት፤ በጤና በግብርናና በሌሎች ዘርፎች የተሻለ ስራን ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ለመስራት በሚያስችለው ሁኔታ ላይ ከሰራተኞቹ ጋር መክሯል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የጅማ ኢንደስትሪ ፓርክ ጎበኙ፡፡

ከጅማ ኢንደስትሪ ፓርክ በተጨማሪ ዱከም ኢንዱስትሪያል ፓርክን ጨምሮ በጅማና በቦንጋ የሚገኙ የጫካ ቡናዎችን ጎብኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ከመጡ ባለሀብቶች ጋር መጎብኘታቸውን የጅማ ከተማ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በጉብኝቱ ወቅትም ባለሀብቶቹ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸውንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል። በ61 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር […]

የኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶች በሀገሪቱ የተከሰቱ ግጭቶች እና እየተባባሰ የመጣውን ስርዓት አልበኝነትን አጥብቀን እናወግዛለን አሉ፡፡

የሀይማኖት አባቶቹ ይህንን ያሉት የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነዉ፡፡ የሃይማኖት አባቶቹ በቅርቡ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጅጅጋ ከተማ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የሰው ህይወት መጥፋቱ እና አብያተ ክርስቲያናት መቃጠል የትኛውንም ሃይማኖት የማይወክል ኢ ሰብዓዊ ድርጊት ነዉ ብለዋል፡፡ በተያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው ስርዓት አልበኝነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጹት የሃማኖት አባቶቹ […]

ኢትዮጵያ ከቱሪስቶች 3. 5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር አገኝች፡፡

የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት በ2010 ዓ.ም ኢትዮጵያን ከጎበኙ 934 ሺ ቱሪስቶች 3.5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡ ከጎብኝዎች መካከል የቻይና ቱሪስቶች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ሲሆን፤ የእንግሊዝ እና የአሜሪካን ዜግነት ያላቸዉ ቱሪስቶችም በብዛት ሀገራችንን ጎብኝተዋል፡፡ ለገቢዉ መገኘት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከባለድርሻ አካላትጋር ዘርፉን ለማሳደግ በጋራ መስራቱና የኢትዮጵያ […]

የቡሄ ባህል መሰረታዊ ይዘቱን መቀየሩ አሳስቦኛል አለ::

ይህንን ያለዉ የአዲስ አበባ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ነዉ፡፡ በባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የጋራ ባህል እሴትዳይሬክተር አቶ አለማየው ጌታቸው የቡሄ ባህል መሰረታዊ ይዘት እየተቀየረ መምጣቱንና ስነቃሎቹም ላይ ጥናት ሊደረግ መሆኑን ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ባህል እና ቱሪዝም ቡሄን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለማደረጉን ገልፀው በመጪው ቡሄ ስነቃላዊ ጥናቶችን ለማድርግ በፌደራል ደረጃ መስሪያ ቤቱ […]