loading
ሩስያ በሺዎች ሚቆጠሩ የሰሜን ኮሪያ ዜጎች በሀገሯ ገብተዉ እንዲቀጠሩ ፈቀደች፡፡

ሞስኮ ታይምስ ከመቀመጫዉ ከሞስኮ እንደዘገበዉ በሩሰያ ከ10 ሺ በላይ ሰሜን ኮርያዉያን የስራ ፍቃደ ማግኘታቸዉን አረጋግጠዋል፡፡ ሩስያ የወሰደችዉ እርምጃ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፒዮንግያንግ ዜጎች ላይ ከሀገር ወጥተዉ እንዳይሰሩ የተጣለባቸዉን ማእቀብ የጣሰ ነዉ ተብሏል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ጉዳዩን እያጣራሁ ነዉ ብሏል፡፡ ሩስያ ግን ስለጉዳዩ ለማንም ምላሽ አልሰጠችም፡፡ እስካሁን ሩስያ ዉስጥ የሚኖሩ ሰሜን ኮርያዉያን ወደሀገራቸዉ በየአመቱ እስከ 300 […]

በሰኔ 16 የቦምብ ፍንዳታ ከተጠረጠሩት ግለሰቦች መካከል በአምስቱ ላይ ክስ ሊመሰረት ነው::

ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ድጋፍ ለመስጠት ሰኔ 16 ቀን 2010 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀ ሰልፍ ላይ ቦምብ በማፈንዳት ከተጠረጠሩ ግለሰቦች መካከል በአምስቱ ላይ ክስ ሊመሰረት ነው። መርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ያሰረከበባቸው ተጠርጣሪዎች አብዲሳ ቀነኔ፣ ደሳለኝ ተስፋዬ፣ ጌቱ ግርማ፣ ህይወት ገዳ እና ባህሩ ቶላ ናቸው። የፌደራል ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች […]

ኢትዮጵያ ለሽምግልና ልትቀመጥ ነዉ፡፡

ኢትዮጵያ የምትሸመግለዉ ኤርትራንና ጅቡቲን ነዉ፡፡ የዉጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም በሰጡት መግለጫ በሁለቱ ሀገራት መሀከል ያለዉ ችግር ተቀርፎ ሰላማዊ ግንኙነት እንዲሰፍን ኢትዮጵያ ለጅቡቲዉ ፕሬዝዳንት መልክት ልካለች ብለዋል፡፡ ሁለቱ ሀገራትም ለሽምግለና ለመቀመጥ መልካም ፍላጎትን አሳይተዋል ተብሏል፡፡

ለህፃናት ሞት መቀነስ ዋና መፍትሄ ጡት ማጥባት ነው ተባለ ፡፡

ይህ የተባለው አለም አቀፍ ጡት የማጥባት ሳምንትን በተመለከተ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ላይ ነው፡፡ አለም አቀፍ የጡት ማጥባት ሳምንት በኢትዮጲያ ሲከበር ለ10ኛ ጊዜ ሲሆን “ጡት ማጥባት የሕይወት መሰረት ነው” በሚልመሪ ቃል እስከ ነሃሴ 1ቀን 2010 ዓ.ም ይከበራል ፡፡ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የእናቶች እና ህፃናት ዳይሪክቶሬት የስርአዓተ ምግብ አማካሪ ወ/ሮ በላይነሽ ይፍሩ ህፃናት ከወሊድ […]

በድሬዳዋ ሲካሄድ የቆየው የሶማሌ ክልል የህዝብ ተወካዮች የጋራ የምክክር መድረክ የህዝቦችን ሃሳብ ያንጸባረቀ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ።

በድሬዳዋ ሲካሄድ የቆየው የሶማሌ ክልል የህዝብ ተወካዮች የጋራ የምክክር መድረክ የህዝቦችን ሃሳብ ያንጸባረቀ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ። ለሶስት ቀናት በቆየውና የሶማሌ ክልል ህዝብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አጀንዳውን አድርጎ ሲካሄድ የቆየው ስብሰባ ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል። የክልሉ የህዝብ ተወካዮች በክልሉ በሰው ህይዎት እንዲሁም በመንግስት ንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን በመግለጽ ድርጊቱ በአስቸኳይ ሊቆም […]

የ ኮድ 3 አጋዥ ታክሲ ባለቤቶች በሰልፍ አቤቱታ እያቀረቡ ነው ።

“ጥያቄአችን ካልተመለሰ ስራ እናቆማለን” ብለዋል ። በአዲስ አበባ ከተማ በአጋዥ ታክሲ ትራንስፖርት አግልግሎት ላይ የተሰማሩ ኮድ 3 ሚኒባስ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች 22 አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ፅህፈት ቤት ፊትለፊት አቤቱታ ለማቅረብ ስራ አቁመው ተሰልፈዋል። የተቃውሞው መነሻ “የተተመነው የታክሲ ታሪፍ ከተሰጠን ስምሪት ርቀት ጋር ባለመጣጣሙ ለኪሳራ እየዳረገን ስለሆነ ይሻሻልልን” የሚል ነው። በአሁኑ ሰአት በመቶዎች የሚቆጠሩ […]

ሱዳንና ኢትዮጵያ የድንበር ቁጥጥርን ለማስወገድ ተስማሙ::

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር የምታደርገውን ቁጥጥር ለማቆም ቁርጠኛ መሆንዋን አስታውቃለች፡፡ ሱዳን ከውሳኔ ላይ የደረሰችው የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሀፊዝ አብዱል ራህማን ከኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በካርቱም በገቡት ስምምነት መሰረት ነው፡፡ የሀገራቱን ግንኙነት እንደሚያጠናክር የተነገረለት ስምምቱ እውን የሚሆነውም በሁለቱ ሀገራት የጋራ የቴክኒክ ኮሚቴ አማካኝነት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ ሹም ሽር ሊያካሄድ ነው ተባለ፡፡

ሪፖርተር እንደዘገበዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የካቢኔ አባላት ሹም ሽር ሊያካሂዱመሆኑ እና ከመጠን በላይ በመስፋታቸው ምክንያት ለአሠራር አላመቹም የተባሉ መሥሪያ ቤቶች እንደሚታጠፉ ተነገሯል፡፡ ከፌዴራል መንግሥትና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ አመራሮች፣ እስከ ቀጣዩ ምርጫ ድረስ የካቢኔ አባል ሆነው የሚሠሩ ተሿሚዎች እየመለመሉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር […]