የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስራ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ለተጨማሪ ምርመራ ከፖሊስ ከተጠየቀው 14 ቀን 8 ቀን ፈቀደ፡፡
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስራ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ለተጨማሪ ምርመራ ከፖሊስ ከተጠየቀው 14 ቀን 8 ቀን ፈቀደ፡፡
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስራ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ለተጨማሪ ምርመራ ከፖሊስ ከተጠየቀው 14 ቀን 8 ቀን ፈቀደ፡፡
መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገው ዘ በርንተስት የተባለዉ ፋውንዴሽን የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝን የአማካሪ ቦርድ አድርጎ መሾሙን ኦል አፍሪካን ዶት ኮም ዘግቧል፡፡ ፋውንዴሽኑ የአፍሪካን ኢኮኖሚ በአዲስ አስተሳሰብ እና በአዳዲስ ግኝቶች ለማጠናከር የተቋቋመ ነው፡፡
የደቡብ ኮርያው ፕሬዝዳንት ለዓመታት በግጭት ውስጥ የቆዩትን ሴኡልና ፒዮንግያንግን የሚያገናኝ የባቡር መስመር ግንባታ ለማካሄድ እቅድ ይዘዋል፡፡ ምንም እንኳ በደቡብና ሰሜን ኮርያ መካከል የፖለቲካ ውህደት ለማድረግ ጊዜ የሚፈልግ ጉዳይ ቢሆንም በትራንስፖርት ቢተሳሰሩ ኢኮኖሚያቸውን ከማሳደግ አልፈው የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች እርስ በርስ እንዲቀራረቡ በር ይከፍታል ብለዋል ሙን ጃይ ኢን፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ፕሬዝዳንቱ ተግባራዊ እንዲሆን ያሰቡት “ሬይልሮድ ኮሚዩኒቲ” የተሰኘው […]
የሞት ፍርዱ የተላለፈባቸው ሰዎች ታጣቂዎች ሲሆኑ በፈረንጆቹ 2011 ትሪፖሊ ውስጥ የቀድሞውን የሀገሪቱ መሪ ሙአመር ጋዳፊን በተቃወሙ ሰዎች ላይ ተኩስ ከፍተው በመግደላቸዉ ነዉ፡፡ የሞት ቅጣት ከተላለፈባቸዉ ዉስጥ የሙአመር ጋዳፊ ልጅም ይገኝበታል ተብሏል፡፡ በሊቢያ ከጋዳፊ አገዛዝ መውደቅ በኋላ በርካታ ወንጀለኞች የሞት ቅጣት ቢተላለፍባቸውም በቁጥር ደረጃ ግን የአሁኑ ትልቁ ነው፡፡ የሞት ፍርድ ከተላለፈባቸዉ ሌላ ከ54 የሚበልጡት ላይ የአምስት […]
አዲኃን ባለፉት ስምንት ዓመታት መቀመጫውን ኤርትራ አድርጎ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስርዓት በመቃወም የትጥቅ ትግል ሲያደርግ የነበረ የፖለቲካ ፓርቲ ነዉ፡፡ የአማራ መገናኛ ብዙሃን እንዳስታወቀዉ አዲኃን ከመንግስት ጋር የሚያደርገዉ ድርድር ምን ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር አስካሁን አልታወቀም፡፡ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ትላንት አስመራ መግባታቸዉ ይታወሳል፡፡
ይህን ያለው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ከሚሽን በቢሸፍቱ ከተማ ለፌደራልና ክልል የጸጥታ ተቋማት ሀላፊዎች ባዘጋጀዉ ስልጠና ላይ ነዉ ። ስልጠናው በአትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶችን ማክበርና ማስከበር ላይ ያተኮረ ሲሆን ለአምስት ቀናት የሚሰጥ ነው ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገብረእግዚአብሄር ስልጠናዉን ሲከፍቱ ሰልጣኞቹ ሰብዓዊ መብት መከበርና ማስከበር ላይ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል ። ስልጠናው […]
በአገራችን 2010 ዓ.ም 40ሺህ 998 የተሸከርካሪ አደጋ ደርሷል፡፡ 5ሺህ 118 ሰዎች በተሸከርካሪ አደጋ ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል፡፡ 7ሺህ 754 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 7ሺህ 775 ሰዎች ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከ 920 ሚሊዮን 771 ሺህ ብር በላይ የተገመተ ንብረት ወድሟል፡፡ ባለፈው ዓመት 2009ዓ.ም የደረሰው አደጋ 38ሺህ 737 ነበር፡፡ አቶ ይግዛው ዳኘው የትራንስፖርት ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት […]
የሰላም ኮንፍረንሱ የተካሄደው በአዲስ አበባ የኢሲኤ አዳራሽ ነው፡፡ አለም አቀፍ የሴቶችና ወጣቶች የሰላም ኮንፈረንስ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ስለሰላም የሚያወሳ አጫጭር ጹሁፎችን አቅርበዋል። ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሴቶች እና ወጣቶች ለሰላም መረጋገጥ […]
“የአዲስ ተስፋ ቀመር” በሚል መሪ ቃል የ2011 አዲስ አመት በአል በተለያዩ መርሀ ግብሮች በአዲስ አበባ ይከበራል ተባለ።
የውይይት መድረኩ የፊታችን እሑድ ነሐሴ 13 ቀን ይካሔዳል፡፡ በትግራይ ክልል የፖሊሲ ጥናት ተቋም ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፍሰሃ ሀብተ ፂዮን እንደተናገሩት የውይይት መድረኩ የመለስ ዜናዊ ስራዎች ላይ የሚያተኩር ሲሆን የሃገሪቱ የህዳሴ ጉዞ እንዲሁም ወቅታዊ ሁኔታዎች ይዳሰሱበታል፡፡ የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ ዶ/ር ፍሰሀ በመድረኩ ነባር እና አዲስ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ምሁራን፣ፖለቲከኞች፣የተለያዩ ድርጅት ተወካዮች እነዲሁም የመቀሌ ከተማ እና […]