loading
በፍቅር እንደመር በይቅረታ እንሻገር በሚል መሪ ቃል ጳግሜ 5 ቀን የአዲሱን አመት መግቢያ በማስመልከት አዲስቷን ኢትዮጵያን ለመገንባት ቃል የመግባት ፕሮግራም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳች ፅህፈት ቤት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ካሣሁ ጎርፌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በዝግጅቱ አድስቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት የሚያስችለንን ቃል የምንገባበት ከመሆኑም በላይ በሁለም የህብረተሰብ ከፍል እና በመላው ሀገሪቱ የመነቃቃት ስሜት በሚፈጠርበት በመደመር ስሜት በውጭ ሀገር የሚኖሩትን ጨምሮ አዲሲቷ ኢትዮጵያ በጋራ የምንገነባበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በዝግጅቱ ከ 2 መቶ በላይ ኤርትራውያን ለመጋበዝ ከውጭ ጉዳይ ጋር በጋራ በመሆን […]

ቴል አቪቭ ከዋሽንግተን ሌላ ውለታ እየጠበቀች ነው፡፡

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤናሚን ኔታናያሁ እራኤል ከሶሪያ በሀይል የወሰደችውን የጎላን ተራራን የባለቤትነት እውቅና እንድትሰጣት አሜሪካን አጥብቀው ጠይቀዋል፡፡ ከአሁን ቀደም እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ናት የሚለውን ውሳኔ ያሳለፈው የትራምፕ አስተዳደር አሁን ደግሞ ለጎላን ተራራ ሌላ እውቅና እንዲሰጠን የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን ብላል ኔታናያሁ፡፡ ኔታናያሁ ይህን ያሉት የአሜሪካው የደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን ሀገራቸው እስካሁን የጎላን ተራራ ለእስራኤል ይገባታል […]

የአቃቂ ግድብ መሙላት አደጋ ስለሚያስከትል የማስተንፈስ ስራ አሁንም ይቀጥላል ተባለ፡፡

ይህንን ያለዉ የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ነዉ፡፡ በባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሄደት መሪ አቶ እስጢፋኖስ ብስራት ለአርትስ ቲቪ በትላንትናው ዕለት አቃቂ አካባቢ የደረሰውን የጎርፍ አደጋ ተከትሎ በተለያዩ ማህበራዊ ድረገፆች ላይ የአቃቂ ግድብ ሞልቶ ለማስተንፈስ በተደረገ ጥረት ውስጥ ቸግሩ እንደተከሰተ እና የሚመለከተውም አካል ማስጠንቀቄያ እንዳልተሰጠ ተደርጎ ሲነገር የነበረዉ ሀሰት ነዉ ብለዋል፡፡፡ በክረምት ሁሌ የማስተንፈስ ስራ […]

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ብአዴን ወደፊት የሚመራባቸውን የፖለቲካ መስመሮች ለመወሰን እየመከረ ነው፡፡ 

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ይመራበት የነበረውን አብዮታዊ ዲሞክራሲ እናሻሽል ወይም አናሻሸል በሚሉ እና ሌሎች መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው፡፡ በዋናነትም አብዮታዊ ዴሞክራሲን እናሻሽል ወይም አናሻሸል? በሚል መሰረታዊ የማሻሻያ ጉዳዮችይወያያል፡፡ የድርጅቱ ስያሜ እና ዓርማ የአማራን ህዝብ አይወክልም በመባሉም ይመከርበታል፡፡ ድርጅቱ ባለፉት ጊዜያት ይመራባቸው የነበሩ ህጎች አንዳንዶቹ ወቅቱን ያላገናዘቡ በመሆኑ ይመከርባቸዋል፡ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በክልሉ ካሉ አመራሮች የሰበሰባቸውን […]

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል 11 ዞኖች ከተውጣጡ የሴቶችና ወጣቶች ተወካዮች፣ ምሁራንና ከተለያዩ የአለም አገራት ከመጡ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በክልሉ ወቅታዊና የለውጥ እንቅስቃሴዎች ላይ እየተወያዩ ነው።

  ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል 11 ዞኖች ከተውጣጡ የሴቶችና ወጣቶች ተወካዮች፣ ምሁራንና ከተለያዩ የአለም አገራት ከመጡ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በክልሉ ወቅታዊና የለውጥ እንቅስቃሴዎች ላይ እየተወያዩ ነው። ምንጭ ኢቢሲ  

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት አለን አሉ ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ፡፡

  አርትስ 18/12/2010 የአሜሪካ ኮንግረንስ አባላት ልኡካን ቡድን ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይቷል፡፡ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ ኮንግረንስማን ክሪስ ስሚዝ አሁን እየተካሄደ ያለው ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጠል ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ዕድገት ለምታደርገው አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡ የአሜሪካ ኮንግረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀው […]

ዶክተር አብይ አህመድ ከአሜሪካዉ ኮንግርስ አባል ክሪስ ስሚዝ ጋር ተወያዩ፡፡

አርትስ 18/12/2010 የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጽህፈት ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በቲዉተር ገጻቸዉ እንዳስታወቁት ሁለቱ ወገኖች ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ዶክተር አብይም ለክሪስ ስሚዝ በሀገሪቱ ያሉ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለዉጦች ላይ ማብራርያ ሰጥተዋቸዋል፡፡  

በትምህርት ሚኒስቴር ፍኖተ ካርታ ላይ የተካሄደዉ የሶስት ቀን ዉይይት ዉጤታማ እንደነበር ትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ  በቲዉተር ገጻቸዉ ገለጹ፡፡

አርትስ 18/12/2010 ዶክተር ጥላዬ በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርትና ሥልጠና ዘርፉ የቀጣዩን 15 ዓመታት ፍኖተ-ካርታ ላይ በተደረገዉ ውይይት ፍኖተ ካርታዉን የሚያዳብሩ ሀሳቦች ተገኝተዉበታል ብለዋል፡፡ ምኒስትሩ አሁን ያለዉ ፍኖተ ካርታ በረቂቅ ደረጃ መሆኑን ማሳሰብ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከቬትናሙ ፕሬዚዳንት ትራን ዳይ ኩአንግ ጋር ተወያዩ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በቲዉተር ገፃቸው አንዳስታውቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ   ፕሬዝዳንት ትራን ዳይኩአንግን በፅህፈት ቤታቸዉ ተቀብለዉ አነጋግረዋቸዋል፡፡ መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት ባህል፣ ኢኮኖሚ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡  በተጨማሪም በኢንቨስትመንት እና በቪዛ አገልግሎት ሁለቱ ሀገራት ተባብረው መስራት የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡ የቬትናሙ ግሬዝደንት በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ […]