loading
በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የሕግ የበላይነት ለማስከበር ሕጋዊ እርምጃዎች ተወሰዱ።

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የሕግ የበላይነት ለማስከበር ሕጋዊ እርምጃዎች ተወሰዱ። ሱሉልታ በቄሮ ስም እንቅስቃሴ በማድረግ ሌሊት የግለሰቦችን ቤት በማፍረስና ቆርቆሮ በመውሰድ ላይ የተሰማሩ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ሻሸመኔ ባለፈው ሳምንት በከተማው የተፈጸመው ወንጀል እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 7 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ቡራዩ የቄሮ አመራር ነኝ በማለት መታወቂያ አዘጋጅቶ የተለያዩ ተቋማት በግድ ስፖንሰር እንዲያደርጉት […]

የአሸንዳ ክብረ በአል ከባህላዊ እሴትነቱ ባሻገር ለነጋዴዎች የገቢ ማስገኛ መንገድ ነው ።

አርትስ ቲቪ በመቀሌ ከተማ ያነጋገራቸው ነጋዴዎች በአሸንዳ በአል ነጋዴዎች ልጃገረዶች የሚለብሷቸውን ባህላዊ አልባሳት፣ፀጉርላይ የሚታሰሩ (እንቁ)የሚባሉ ማጌጫዎች ፣ በቀሚስ ላይ የሚደረግ የተገመደ ክር (ድሪ) የአንገትና የጆሮ ጌጣጌጦች በአዘቦቱ ቀን ከሚሸጡበት የ20 እና 30 ብር ጭማሪ አንዳለው ነው የተናገሩት። በአሉን ልጃገረዶች በተለየ መንገድ ስለሚያከብሩት የፀጉር ባለሙያዎችንም ትርፋማ የሚያደርግ እንደሆነ ተመልክተናል ።

በነገው እለት የሚከበረውን የአሸንዳ በአል አስመልክቶ በመቀሌ ከተማ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

የፓናል ውይይቱ አብይ አላማ ያለፉት አመታት የበዓሉን አከባበር መገምገም፣አሸንዳን በአለም አቀፍ ደረጃ ስለማስተዋወቅ እንዲሁም ከዩኔስኮ ጋር የተያያዙ ጥናቶች እና ሀሳቦችን ማንሳት ነው ተብሏል፡፡ የትግራይ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ ዘነቡ ሐለፎም እንደገለፁት አሸንዳ ከባህላዊ እና ሃይማኖታዊ አንድምታው በተጨማሪ ለሴቶች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትስስር እንዲሁም ፖለቲካዊ ተሳትፎአቸውን የሚያሳይ የነጻነት ቀን ነው ብለዋል፡፡ በውይይቱ የቀደሙ […]

ተወረወረች ጨረቃ …በመድሃኒዓለም ጫንቃ

ተወረወረች ጨረቃ በመድሃኒዓለም ጫንቃ . ይሄ አዳራሽ ….ኧኸ የማን አዳራሽ የጌታዬ ድርብ ለባሽ። . ይኸው ሲዞር ወገቧ ባቄላ ነው ቀለቧ . ይሄው ወገቤ ነጭ ጤፍ ነው ቀለቤ። በሚለው የልጃገረዶች ጨዋታ ለሚደምቀው አሸንድዬ በላሊበላ ዝግጅት እየተደረገ ነው።