loading
ከስድስት ወራት በኋላ የሁሉም የስኳር ፕሮጀክቶች ግንባታ እንደሚጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ዶክተር አብይ ይህንን ያሉት በባህርዳር ከተማ ከብአዴን አመራሮች ጋር ባደረጉት ምክክር ላይ ነው፡፡ ባለፉት 9 ወራት የተሻለ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠርና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን ለማምጣት ውጤታማ ተግባራት ተከናዉነዋል ብለዋል፡፡ በሀገሪቱ የተሻለ መግባባት ለመፍጠርም ከዲያስፖራው ማህበረሰብ ጋር የነበረውን ግንኙነት የማስተካከልና በሀይማኖቶች ውስጥ የነበረውን መከፋፈል የማጥፋት ስኬታማ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡ በኢኮኖሚ ረገድም የውጭ ምንዛሬ በቤታቸው ያከማቹ ዜጐች ወደ ባንክ […]

ባለፉት 24 ዓመታት በኢትዮጵያ በትምህርትና ስልጠና ሥርዓት በታዩ ችግሮች ዙርያ ዛሬ ውይይት ይደረጋል

የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ከዛሬ ጀምሮ የሚደረገው የውይይት መድረክ ዋነኛ ዓላማ ለፍኖተ-ካርታው ዝግጅት እንዲረዳ በተዘጋጀው የመጀመሪያ ደረጃ ረቂቅ ጥናት ዙሪያ ውይይት በማድረግ ለፍኖተ-ካርታው ዝግጅት የሚረዳ ተጨማሪ ግብዓት ለማሰባሰብ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ የማሻሻያ ሀሳቦች ዙሪያ በሚደረገው ውይይት በተሳታፊዎች የሚቀርቡ ተጨማሪ የማሻሻያ ሀሳቦች በቂ ውይይት ከተደረገባቸውና መግባባት ከተደረሰባቸው በኋላ ለ15 ዓመታት […]

የዘንድሮ አረፋ በዓል በአዲስ አበባ በአንድነት በአንድ ቦታ በስቴዲም ይከበራል፡፡

በነገው ዕለት የሚከበረው ዒድ አል አድሃ አረፋ ከሌሎች ግዜያቶች በተለየ መልኩ በአንድነት እና በፍቅር ስሜት እንድሚከበር ነዉ የአድስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክርቤት ፕሬዝደንት ሼህ መሀመድ ሸሪፍ ሃሰን ለአርትስ ቲቪ የተናገሩት፡፡ የዘንድሮው አረፋ ልዩነታችን ተገፎ በአንድነት እና በእርቅ ማከበራችን ለየት ያደርገዋል ብለዋል፡፡ በዓሉም ‹ሰላም እና አንድነት ለኢትዮጵያ›› በሚል መሪ-ቃል እንደሚከበርም ሼህ መሀመድ ነግረዉናል፡፡ የ አረፋ […]

የቀድሞው የጃኮቭ ዙማ አስተዳደር ምርመራ ሊደረግበት ነው፡፡

ደቡብ አፍሪካ በፕሬዝዳንት ጃኮቭ ዙማ ዘመነ መንግስት የተፈጸመውን የሙስና ወንጀል ለማጣራት አዲስ ምርመራ ልትጀምር ነው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው የሀገሪቱ የፍትህ ተቋም በወቅቱ በመንግስት ተቋማት ላይ የተፈጸሙትን የሙስናና የማጭበርበር ወንጀሎች ለማጣራትና በድርጊቱ የተሳተፉትን ለፍርድ ለማቅረብ የሚደረገውን ስራ ዛሬ በይፋ ይጀምራል፡፡ ፕሬዝዳንት ጃኮቭ ዙማ ከአሁን ቀደም በስልጣናቸው እያሉ በሙስና ቅሌት ተጠርጥረው ተደጋጋሚ ክስ ይቀርብባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

በትምህርት ፖሊሲያችን ላይ ሁሉን አቀፍ ለዉጥ እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

በትምህርት ፖሊሲያችን ላይ ሁሉን አቀፍ ለዉጥ እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በቲዉተረ ገጻቸዉ እንዳስታወቁት ዶክተር አብይ ይህንን የተናገሩት ዛሬ የተጀመረዉን ሀገር አቀፍ የትምህርት ፖሊሲ ማሻሻያ ፍኖተካርታ ፎረምን በንግግር በከፈቱበት ወቅት ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ማሻሻያ ተደረገበት፡፡

በዚህም መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ባለስልጣኑ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ላይ ብቻ እንዲያተኩርና ቀደም ሲል በባለስልጣኑ ይሰጡ የነበሩ ሌሎች አገልግሎቶች ወደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ሌሎች ተጠሪ ተቋማት እንዲዛወሩ መደረጉን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን በቲዉተርና በፌስቡክ ገጻቸዉ አስታዉቀዋል፡፡ በቀጣይም የስራ ኃላፊዎች፣ሰራተኞችና የአሰራር ስርዓቱ ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን በማለት ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት በተያዘው አቅጣጫ መሰረት […]

አርሷደሯ ጌሪ አሜሪካ ተብሎ ለሚጠራው የእህል ፈጅ ትል መድሀኒት አገኙ፡፡

አርሷደሯ ወ/ሮ ታቦቴ አባተ በቦኖ በደሌ ዞን አርሶ አደር ናቸው። ከችግራቸው በመነሳትም ጌሪ አሜሪካ ለተባለ ትል አዲስ የትል ማጥፊያ ፈጥረዋል። የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ሴንተር በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ ጌሪ አሜሪካ በቆሎን በብዛት የሚያጠቃ ትል ነው።ትሉ ቁጥጥር ካልተደረገበት በበቆሎ ምርት ላይ ከባድ ጉዳት ያደርሳል። በአንድ ሌሊት በ1500 እጥፍ ሊራባ ይችላል። ወ/ሮ ታቦቴ ታዲያ ይህን ትል የሚገድል መድሀኒት […]

ቦኮሃራም በናይጄሪያ 19 ሰዎችን ገደለ።

ፕሬስ ቴሌቭዥን እንደዘገው ታጣቂው ቡድን ቦኮሃራም በሰሜን ምዕራብ የሃገሪቱ ክፍል በምትገኘው ማይላሪ ዘልቆ በመግባት በተሽከርካሪ የታገዘ የሮኬት ጥቃት ፈፅሟል። ማንነታቸው ያልተገለፀ የእርዳታ ሰጭ ድርጅት ሰራተኞች የሟቾችን ቁጥር 63 አድርሰውታል። የአካባቢው ነዋሪዎች ፖሊስ ጥቃቱ ሲፈጸም ህዝቡን ለመከላከል ምንም ዓይነት ሙከራ ባለማድረጉ ማዘናቸውን ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡ ቦኮሃራም ከፈረንጆቹ 2009 ጀምሮ እስካሁን ከ20 ሺህ በላይ ናይጄሪያውያንን ሲገድል፥ […]

የሀጂ ተጓዦች ከከባድ ዝናብ ጋር እየታገሉ ነው፡፡

ማንኛውም ሙስሊም በህይዎት ዘመኑ አንድ ጊዜ ሊያሳካው የሚመኘውን የሀጂ ስነ ስርዓት ለመታደም ከ2 ሚሊዮን በላይ አማኞች ሳውዲ አረቢያ ገብተዋል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው እምብዛም ዝናብ በማታውቀው ሳውዲ አረቢያ እየዘነበ ያለው ነጎድጓዳማ ዝናብ የጎርፍ አደጋና ውሀ ወለድ በሽታ እንዳያደስከትል ተሰግቷል፡፡ የሀገሪቱ የጤና ሚንስቴር ግን እስካሁን ምንም ዓይነት ችግር አላጋጠመም የታየ የህመም ምልክትም የለም የሚል መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ህንድ ባጋጠማት የጎርፍ አደጋ የሟቾችና የተፈናቃዮች ቁጥር ጨምሯል፡፡

ህንድ ባጋጠማት የጎርፍ አደጋ የሟቾችና የተፈናቃዮች ቁጥር ጨምሯል፡፡ በክፍለ ዘመኑ አስከፊ የተባለለት ጎየርፍ አደጋ ያጋጠማት ህንድ 350 ዜጎቿ ለህልፈት ሲዳረጉ ከ800 ሽህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተፈናቅለዋል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ኬራላ በተባለችው የደቡባዊ ህንድ ግዛት የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ህይዎታቸው አደጋ ላይ ያሉ ዜጎችን ለመታደግ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አሁንም ጥረታቸውን ቀጥለዋል፡፡ በግዛቷ የሚገኙ […]