loading
የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ኮፊ አናን በ80 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ ።

የኖቤል ተሸላሚ የነበሩት አናን እአአ በ1938 በጎልድ ኮስት ጋና ነበር የተወለዱት። ኮፊ አታ አናን ሙሉ ስማቸው ሲሆን አካን በሚባል ቋንቋ የመጀመሪያ ስማቸው ‘‘በዕለተ አርብ የተወለደ’’ ማለት ሲሆን አታ ማለት ደግሞ ‘‘መንትያ’’ ማለት ነው። በጋና እና አሜሪካ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ሲሆን የመጀመሪያ ስራቸውን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በመጀመር ለአርባ ዓመታት አገልግለዋል። የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ ለመሆንም በቅተዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋለው የመንጋ ፍትህ እና አላስፈላጊ ሁከት ተቀባይነት የሌለው እና የህግ የበላይነትን አደጋ ውስጥ የሚጥል መሆኑን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በ11ኛው እነ 12ኛው ዙር የሰለጠኑ የመከላከያ መኮንኖችን ባስመረቁበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ነው። በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ድርጊቱ የህግ የበላይነትን የሚነድ በመሆኑ በአስቸካይ ሊቆም እንደሚገባው ገልጸዋል። ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ የተሳሳተ መረጃን መሰረት በማድረግ ለህግ ቅድሚያ ሳይሰጥ የሚፈጽማቸው ድርጊቶች እየተገነባች ያለችን ሃገር ከማፍረስ ውጭ ዋጋ እንደሌለውም ጠቅሰዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ የህግ የበላይነት ለአንድ […]

ከሁለት ሳምንት በፊት ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ፍቃድ ውጭ ገብተዋል የተባሉ አርባ አምስት የፌደራል ፖሊስ ፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል አባላት ከመቀሌ እንዲመለሱ ተደርገዋል

አባላቱ በአሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የመጡበት አላማም እስኪታወቅ ድረስ እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ በፌደራል ካምፕ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርጎ ነበር። የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ረዳኢ ኃለፎም ከክልሉ አቅም በላይ የሆነ የፀጥታ ችግር ባለመኖሩ የፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል አስፈላጊ አለመሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጨምረውም ክልሉ ድጋፍ የሚጠይቀው ከክልሉ አቅም በላይ የሆነ ነገር ሲያጋጥም ወይም […]