loading
ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ፡፡

በኮንስትራክሸን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት በዋና ዳይሬክተርነት እንዲሁም በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮንትራት አስተዳደር እና በምህንድስና ግዢ ላይ በሃላፊነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ኃላፊው በቅርቡ የኢትዮጲያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙትን እና የቀድሞ የተቋሙን ኃላፊ ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝን በመተካት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ይመራሉ፡፡ የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት እንዳስታወቀው የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ እና በከተማዋ የመንገድ መሰረተ […]

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ጋር በጅቡቲ ተወያዩ።

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፥ በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ መካከል ያለው ግንኙነት በሁኔታዎችና በአጋጣሚ የማይለወጥ ስትራቴጂካዊ ወዳጅነት ነዉ ብለዋል፡፡ ዶክተር ወርቅነህ፥ በድሬዳዋ በተፈጠረው ክስተት የጅቡቲ ዜጎች ህይወታቸውን በማጣታቸው ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡ የተፈጠረው ክስተት የሁለቱን ህዝቦች አጠቃላይ ግንኙነት አያሳይም ያሉት ዶክተር ወርቅነህ፥ ጥፋተኞቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ በመሆኑ በሕግ ተገቢውን […]

በ2019 የታዳጊዎች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ፡፡

በማጣሪያው የመጀመሪያ ጨዋታው የኡጋንዳ ቡድንን 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን በሁለተኛ ጨዋታው ጅቡቲን 4 ለ 0 በመርታት ወደ ተከታዩ ደረጃ ለማለፍ የሚያደርገውን ጉዞ አሳምሯል፡፡ የቀይ ቀበሮዎቹን የድል ጎሎች በየነ ባንጃ፤ በረከት ካሌብ፤ ቢንያም አይተን፤ መንተስኖት እንድርያስ አስቆጥረዋል፡፡ እዚሁ ምድብ ኬንያ ደቡብ ሱዳንን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ በቀጣይ መጭው እሁድ ነሃሴ 13 በቻማዚ […]

የዓለም የጤና ድርጅት የዲሞክራቲክ ኮንጎ ጉዳይ አሳስቦኛል ብሏል፡፡

በሀገሪቱ የተፈጠረው አለመረጋጋት የኢቦላ ቫይረስን ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት አደጋ ላይ ጥሎታል ነው ያለው ድርጅቱ፡፡ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም አሁን በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡ ዶክተር ቴዎድሮስ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተፋላሚ ሀይሎች በአስቸኳይ ተኩስ አቁመው የጤና ባለሞያዎች እንደልባቸው ቫይረሱ ወደተከሰተበት አካባቢ ተንቀሳቅሰው ስራቸውን እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ […]

በአንዳንድ አካባቢዎች እየተፈጠረ ያለው አለመረጋጋት የቱሪዝም ዘርፉ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው ተባለ፡፡

ይህ የተባለው የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ትላንት በመስሪያቤቱ በሰጠው መግለጫላይ ነው፡፤ በመግለጫው የቱሪዝም ዘርፍ ሰላም እና መረጋጋትን የሚሻ ዘርፍ እንደመሆኑ በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተከሰቱት ግጭቶች ቱሪስቶችን እና ትውልደ ኢትዮጲያዊያን ዲያስፖራዎችን የሚያሸሽ ነው ተብሏል፡፡ በባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ፎዚያ አሚን ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈጠረውን ድርጊት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ እንደሚያወግዘው ገልፀው ለሰላም እና መረጋጋት […]

የዓለም ባንክ የፍልስጤም ወጣቶችን የስራ አጥነት ችግር እቀርፋለሁ አለ፡፡

ባንኩ በጋዛ የሚገኙ የፍልስጤም ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር አዲስ ፕጀክት ይፋ አድርጓል፡፡ ለፕሮጀክቱ 17 ሚሊዮን ዶላር የተመደበ ሲሆን በዚሁ ፕሮጀክት ከ400 ሺህ በላይ ወጣቶች ተጠቃሚ የሆናሉ ነው የተባለው፡፡ ወጣቶቹ ወደ ስራው ከመግባታቸው በፊት የክህሎት ስልጠናዎችን እንዲያገኙ የሚደረግ ሲሆን ተቀጥረው ከመስራት ባሻገር የራሳቸውን ገቢ የሚያገኙበት የስራ ዓይነትም ይመቻችላቸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በዋናነት መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የሚሰራ […]

ማርክ ዙከርበርክ ለእግር ኳስ አፍቃሪዎቸ አዲስ የምስራች ይዞ ብቅ ብሏል፡፡

እስካሁን በዓለም ላይ ብዙ ተመልካች ያለውና በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን እግር ኳስን በቀጥታ መከታተል የሚቻለው በቴሌቭዥን ቻናሎች አልያም በዌብ ሳይቶች ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ፌስ ቡክ የራሱን መተግበሪያ ተጠቅሞ የስፔን ላሊጋ ጨዋታዎችን ለደንበኞቹ ለማሳየት ተዘጋጅቷል የሚል ወሬ ተሰምቷል፡፡ ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ከእንግዲህ በቀላሉ መተግበሪያውን ተጠቅመው የስፔን ላሊጋ ጨዋታዎችን በቀጥታ መከታተል ይችላሉ፡፡ ህንድን ጨምሮ […]

አንካራና ዋሽንግተን ብድር በመመላለስ የንግድ ጦርነቱን አጧጡፈውታል፡፡

ቱርክ በአሜሪካ ምርቶች ላይ እስከ 140 በመቶ የሚሆን ታሪፍ ጣለች፡፡ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሀን አሜሪካ በሀገሬ ላይ ያወጀቸው ኢኮኖሚያዊ ጥቃት መልስ ያስፈልገዋል ሲሉም ተደምጠዋል፡ ኤርዶሀን ባለፈው ሰኞ በሰጡት መግለጫ ከእንግዲህ ከአሜሪካ የሚገቡ የኤሌክትኒክስ ምርቶች በቱርክ ገበያ ቦታ የላቸውም ብለው ነበር፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው የቱርክ መንግስት በአሜሪካ ምርቶች ላይ ሌላ ተጨማሪ ታሪፍ ጥሏል፡ በዚህም መሰረት የሲጋራ ምርቶች […]

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስራ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ለተጨማሪ ምርመራ ከፖሊስ ከተጠየቀው 14 ቀን 8 ቀን ፈቀደ፡፡

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስራ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ለተጨማሪ ምርመራ ከፖሊስ ከተጠየቀው 14 ቀን 8 ቀን ፈቀደ፡፡