loading
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዩስን መኖሪያ ቤታቸው ድረስ በመሄድ ጎበኙዋቸው፡፡

በጉብኝቱ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል ተገኝተዋል፡፡ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩም እንዳሉት አቡነ መርቆርዮስን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመሆን በመጎብኘታቸው ከፍ ያለ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት ከአቡነ መርቆርዮስ ጋር ስለይቅርባይነትና ስለፍቅር ተወያይተዋል፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጠቅላይ ሚኒስተሩ አቡነ መርቆርዮስን መኖሪያ ቤታቸው ድረስ ተገኝተው በመጎብኘታቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ባለፉት 26 ዓመታት […]

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 5 የአፍሪካ አየር መንገዶችን በሽርክና ሊያስተዳድር ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም እንደተናገሩት የጊኒ አየርመንገድን በ49 በመቶ፣የዛምቢያ አየር መንገድን በ45 በመቶ፣ እንደ አዉሮፓዉያን አቆጣጠር በጥቅምት የሚጀምረዉን የቻድ አየር መንገድን በ49 በመቶ ድርሻ በሽርክና ሊያስተዳድር ነዉ፡፡ የዛምቢያና የኢኳቶሪያል ጊኒ አየር መንገዶችን ደግሞ የአስተዳደራዊ ስራዉን እንዲሰራ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ተቀብሎ በሽርክና ለማስተዳደር መስማማቱን ነዉ አቶ ተወልደ የገለጹት፡፡

ዛሬ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክያትን በጀዋር መሃመድ የሚመራዉ ቡድን የኦሮሚያ የሚያደርገውን ጉብኝቱን ለጊዜው ማቆሙን ኦ ኤም ኤን ዘገበ።

በዛሬዉ ዕለት በሻሸመኔ ከተማ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርከት ያሉ ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱን አቶ አዲሱ አረጋ የኦህዴድ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አስታውቀዋል። አደጋው የደረሰው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ እና ሌሎች የቡድኑ አባላት አቀባበል ለማድረግ በከተማዋ በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ላይ ነዉ። በአደጋውም እስካሁን የ3 ሰዎች ህይወት […]