loading
በኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ ላይ ጭማሪ ሊደረግ ነው::

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚዎች ላይ የታሪፍ ጭማሪ ለማድረግ አስፈላጊው ሂደት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ማሻሻያው ዝቅተኛ የኃይል ተጠቃሚዎችን አያካትትም ተብሏል፡ ቢቢሲ የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ጌታሁን ሞገስን አናግሮ እንደዘገበዉ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪው በተለያዩ ደረጃዎች አልፎ ተቀባይነት ሲያገኝ ተግባራዊ እንደሚሆን ተናግረዋል። አቶ ጌታሁን የታሪፍ ጭማሪ ማድረግ ያስፈለገበትን ምክንያት ለመጨረሻ ጊዜ የታሪፍ ጭማሪ ተደርጎ […]

የኢንጅነር ስመኘው በቀለን ቤተሰቦችን ለመደገፍ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተዋቅሯል::

በሀይደሮ ፓወር ዙሪያ የሚያጠኑና ከፍተኛ ዉጤት ለሚያገኙ ተማሪዎች ኢንጅነር ስመኘዉ በቀለ አዋርድ በሚል ለመስጠት እቅድ ተይዟል ተባለ፡፡ የኢንጅነር ስመኘው በቀለን ቤተሰቦችን ለመደገፍ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተዋቅሯል:: የመንግስት ኮሙኒኬሽን በድረገጹ እንዳስታወቀዉ ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በመኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ የተገኙትን የኢንጅነር ስመኘው በቀለን ቤተሰቦች መደገፍ የሚያስችል የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተዋቅሯል። ኮሚቴው […]

ኢንዶኔዥያ ዳግም በከባድ ርዕደ መሬት ተመታች፡፡

ኢንዶኔዥያ ዳግም በከባድ ርዕደ መሬት ተመታች፡፡ በዛሬዉ ዕለት ኢንዶኖዥያ ሎምቦክ ደሴት አካባቢ በደረሰ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ በርካታ ቤቶች ፈራርሰዋል፡፡ነዋሪዎችም አካባቢቸዉን ጥለዉ ሸሽተዋል፡፡ በርዕደ መሬቱ መለኪያ 6.2 እንዲሁም 6.9 የሆነ ተከታታይ የመሬት መንቀጥቀጥ በተከሰተባት ኢንዶኔዥያ 156 ሺህ ዜጎች ቤት አልባ ሆነዋል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበዉ እስካሁን በአደጋዉ ሳቢያ 131 ሰዎች ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡ከሟቾቹ በተጨማሪ ከ1ሺህ 400 በላይ ሰዎች ከባድ […]

በቀጥታ የዘር ግብይት ሥርዓት ከ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማዳን ተቻለ፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሚሽን ኤጀንሲ ከግብርና እንስሳት ሃብት ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን የቀጥታ የዘር ግብይት ሥርዓትን በተመለከተ ውይይት አካሂዷል፡፡ የቀጥታ የዘር ግብይት ስርዓት በማስረጽ ከዚህ በፊት በዘር አከፋፋይ እና በአርሶ አደሩ ይደርስ የነበረውን ችግር እና ውጣውረድ በማስቀረት ዘር አምራቹን ከአርሶ አደሩ ጋር በቀጥታ በማገናኝት ይባክን የነበረውን የሰው ጉልበት እና ሃብት ማስቀረት ተችሏል፡፡ የግብርናና አንስሳት ሃብት ሚኒስቴር […]

ሊቨርፑሎች ዓመቱ የኛ ነው እያሉ ነው።

የሊቨርፑል ደጋፊዎች ክለባቸው የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ካነሳ ሃያ ስምንት ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም መጭው ዘመን የኛ ነው በማለት ሊጉ ከመጀመሩ በፊት እየፎከሩ ነው ይላል የ ዘሰን ዘገባ። ይህን ተከትሎም የርገን ክሎፕ ከአምናው ሻምፒዮን ጋርዲዮላ በልጠው ለመገኘት ከአሁኑ ትልቅ የቤት ስራ ይጠብቃቸዋል። ክሎፕ አስተያየታቸውን ሲሰጡም ማንቸተር ሲቲዎች የትኛውንም ክለብ የማሸነፍ ብቃት አላቸው፤ ቢሆንም ግን ከረጅም ጊዜ በኋላ […]

በረሺድ ጥላይብ መመረጥ ዌስት ባንክ ደስ ብሏታል፡፡

በአሜሪካ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሙስሊም ሴት የኮንግረስ አባል በመመረጣቸዉ በዌስት ባንክ ያሉ ቤተሰቦቻቸዉ ደስታቸዉን አየገለጹ ነዉ፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበዉ የጥላይብ ሴት አያት ፣አክስትና እንዲሁም አጎቶችዋ የተሰማቸዉን ደስታ ተሰብስበዉ ገልጸዋል፡፡ አንድ ቀን እንዲህ እንደምታኮራን እናምን ነበር ብለዋል፡፡ የጥላይብ ቤተሰቦች የሚኖሩበት ዌስት ባንክ ከ1967 ጀምሮ በእስራኤል ቁጥጥር ስር ይገኛል፡፡ ቤተሰቡ የጥላይብ የኮንግረስ አባል ሆኖ መመረጥ በአከባቢያቸዉ ስላለዉ ችግር ድምጻቸዉ […]

በአክሱም ጽዮን ለሀገራችን ሰላም ምህላ እየተደረገ ነዉ፡፡

በምህላዉ ከ50 ሺህ ሰዉ በላይ እየታደመ እንደሚገኝ በአክሱም ጺዮን የስብከተ ወንጌል ምክትል ሀላፊ በኩረ ትጉሃን ስቡህ ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡ ከነሐሴ አንድ ጀምሮ የፍልሰታ ጾምን አስመልክቶ የተጀመረዉ ምህላ አስከ ጾሙ ማብቂያ ድረስ ይቀጥላል፡፡፡በአክሱም ፂዮን ሁልጊዜ ወር በገባ ከ1-7 ባሉት ቀናት ምህላ የሚደረግ ሲሆን የፍልሰታ ፆም አስመልክቶ ደግሞ እስከ ጾም ፍቺ ምህላ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በኩረ ትጉሃን የዘንድሮዉን […]

የመን ውስጥ በደረሰ የአየር ጥቃት ህጻናት ህይዎታቸው አልፏል።

ቢቢሲ እንደዘገበው በጥቃቱ አርባ ሶስት ሰዎች ተገድለዋል። ከሞቱት ሰዎች መካከልም አብዛኞቹ ህጻናት መሆናቸውን የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል። የቀይ መስቀል ሰራተኞችም በርካታ ህጻናት ቆስለው ወደ ሆስፒታል መምጣታቸውን ምስክርነታቸውን ሰጠተዋል። የጥምር ሃይሉ ሆን ብሎ ሲቪል ሰዎችን ኢላማ አድርጎ ጥቃቱን እንዳላደርሰ ቢናገርም የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ግን ዓለም አቀፍ ህግን የጣስ ተግባር ሲል ድርጊቱን ኮንኖታል። ለዚህ ማሳያ የሚሆነው […]