loading
ስታን ክሮኤንኬ አርሴናልን ለመጠቅለል አሁንም ጥያቄ አቀረቡ፡፡

በአርሴናል ክለብ ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ ያላቸዉ ግለሰቡ ክለቡን የግላቸዉ ለማድረግ ጥያቄ አቅርበዋል ተብሏል፡፡ ክሮኤንኬ በአርሴን ቬንገር አሰልጣኝነት ዘመን ለበርካታ አመታት ያለዉጤት የዘለቀዉን አርሴናልን ለመግዛት 600 ሚሊየን ፓዉንድ ማቅረባቸዉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ 67 በመቶ የክለቡ ድርሻ ባለቤት የሆኑት አሜሪካዊ ቢሊየነር ከአሁን ቀደም ክለቡን ለመጠቅለል ተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበዉ አልተሳካላቸዉም፡፡አሁንስ ይሳካላቸዉ ይሆን? አርሴናል በመጭዉ እሁድ የመጀመርያ የፕሪሜ ርሊግ ጨዋታዉን […]

የመን አዲስ የፖሊዮ ክትባት ጀመረች፡፡

የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ የክትባት ዘመቻዉ እየተካሄደ ያለዉ ከአለም አቀፉ የጤና ድርጅት፣ ከዩኒሴፍ እና ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነዉ፡፡ አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበዉ በክትባት ዘመቻዉ ከ5 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ይከተባሉ፡፡ ክትባቱ ከ5 አመት በታች ላሉ ህጻናት እንደሚሰጥና ከአሁን በፊት የተከተቡ ህጻናትንም ጭምር እንደሚያካትት ታዉቋል፡፡ በሀገሪቱ ያለዉ የእርስ በእርስ ጦርነት በህጻናት ላይ እያስከተለ ያለዉ ችግር […]

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት ለማ መገርሳ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ወደ አስመራ የተጓዙበት ጉዳይ በስኬት ተጠናቋል ተባለ፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ የሚመራውና የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ የሚገኙበት የልዑካን ቡድን፣ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ- መንበር ኣቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራውና አቶ ኢብሳ ነገዎ፣ ኣቶ አቶምሳ ኩምሳ፣ ኣቶ ቶሌራ አደባ እና ኣቶ ገመቹ ኣያና የሚገኙበት የልዑካን ቡድን ዛሬ በአስመራ ኤርትራ በመገናኘት ወንድማዊ መንፈስ በተንጸባረቀበትና በሙሉ መተማመን በተካሄደ የእርቅ ውይይት ያሉ ስምምነቶችና […]

ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሚሰማሩ 1 ሺህ ወጣቶች በዛሬው ዕለት ገለጻ አድርገዋል

የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከዛሬ ነሐሴ 1 ቀን እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2010 ዓ.ም የሚካሄድ ነው። ዛሬ ይፋ በተደረገው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ላይ ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 1 ሺ ተመራቂ ወጣቶች ተሳታፊዎች ናቸው። ወጣቶቹ ከሚኖሩበት ክልል ባለፈ ወደ ሌሎች ክልሎች በመሄድ በተለያዩ ተግባራት ላይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ይሰጣሉ። ይህ ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች የበጎ […]

አብዲ ሞሃመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

አብዲ ሞሃመድ ዑመር ትናንት ከክልሉ ፕሬዚዳንትነታቸው መነሳታቸው ቢገለጽም የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሪ ሆነው ይቀጥላሉ ተብሎ ነበር። የቀድሞው የክልሉ ፕሬዝዳንት በመከላከያ ሠራዊት አባላት በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ከተደረጉ በኋላ ጅግጅጋ ከሚገኘው ቤተ መንግሥት እንደተወሰዱ ምንጮች ለቢቢሲ ሶማልኛ ገልጸዋል። ከቅዳሜ አንስቶ በጂግጂጋ እና በክልሉ ሌሎች ከተሞች የተከሰተውን ሁከት ተከትሎ የሃገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ወደ […]

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ መጠሪያውን ወደ “ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” ለመቀየር ሀሳብ ማቅረቡ ተገለፀ።

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ መጠሪያውን ወደ “ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” ለመቀየር ሀሳብ ማቅረቡ ተገለፀ። የኦህዴድ የገጠር ፖለቲካና አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንደገለጹት፥ የኦህዴድን የስያሜ እና የአርማ ለውጥ ለማድረግ ሀሳብ ቀርቧል። በዚህም መሰረት አዲሱ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ መጠሪያ “የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” እንዲሆን ሀሳብ መቅረቡን ነው አቶ አዲሱ ያስታወቁት። ከዚህ በተጨማሪም ኦህዴድ ከዚህ […]

ግብጽ ጥንታዊ ቅርሶቿን አስመለሰች፡፡

ግብጽ ከ500 ዓመት በላይ እድሜ ያላቸውን ቅርሶቿን ከእንግሊዝ መረከቧን የሀገሪቱ የባህል ሚኒስትር ኢሳም አብደል ዳይም ተናግረዋል፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ቅርሶቹ የጥንታዊት ግብጽን ታሪኮች የሚያሳዩ የድንጋይ ላይ ጽሁፎችና ስዕሎች ናቸው፡፡ አብደል ዳይም እነዳሉት እነዚህ ጽሁፎች እና ስዕሎች በስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሙህዲን አል ካፊጂ በተባለ ጥበበኛ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ግብጽ ከ50 ዓመት በፊት ከ33 ሺህ በላይ […]