loading
ሐምሌ 28 በሚሌኒየም አዳራሽ የቤተክርስትያን አንድ መሆንን አስመልክቶ ልዩ ጉባዔ ይካሄዳል፡፡

ጉባዔዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አራተኛ ፓትሪያሪክ የሆኑት የብፁዕ አቡነ መርቆሪዎስ አቀባበል አንዱ አካል ነዉ ተብሏል፡፡ የጠቅላይ ቤተክህነት ስራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆሮስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በሚሊኒየም አዳራሽ ሀምሌ 28 ቀን 2010ዓ.ም የሚደረገዉ ጉባዔ የቤተክርስቲያን ልደት በመሆኑ ታላላቅ የሀይማኖት አባቶች፤ ህዝበ ክርስትያኑ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ አምባሳደሮችና የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በጉባኤዉ […]

ጎንደርን ፍለጋ የተሰኘ መጽሀፍ ተመረቀ፡፡

በጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የተጻፈዉ ጎንደርን ፍለጋ የጉዞ ማስታወሻ ትላንት ሲመረቅ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢትዮጵያ የቱሪዝም ድርጅት ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰርፀፍሬ ስብሀት እንደተናገሩት ጋዜጠኛ ሄኖክ የጻፈዉ መጽሀፍ ባህልን ታሪክንና ቱሪዝምን የያዘ ነዉ፤ልንጠቀምብት ይገባል ብለዋል፡፡ ጎንደርን ፍለጋ መጽሀፍ ጋዜጠኛዉ በተለያየ አካባቢዎች ባደረጋቸዉ ጉዞዎች የሰማቸዉን ያያቸዉን ታሪኮች አጣርቶ ያስቀመጠበት ነዉ፡፡ በመጽሀፉ ዉስጥ ጎንደርን ፍለጋ በደጃዝማች አያሌዉ […]

የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ዉጤት ዛሬ ከሰዓት ይፋ ይሆናል፡፡

154 ሺ 10 ወንዶችና 127 ሺ 964 ሴቶች በድምሩ 281 ሺ 974 ተማሪዎች ፈተናዉን ወስደዋል፡፡ ተማሪዎች ዉጤታቸሁን ለማወቅ በኤጀንሲዉ ድረ ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት admission በሚለዉ ዉስጥ የመፈተኛ ቁጥር በመጻፍ go የሚለዉን አንዴ በመጫን ማየት ትችላላችሁ ተብላችኋል፡፡

በምህረት አዋጅ ሰበብ በማረሚያ ቤቶች ተከስቶ የነበረዉ አለመረጋጋት መስከኑን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ ፡፡

የምህረት አዋጁ ከወጣ በኋላ ምህረት ይገባናል በሚል በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ሁከት ተከስቶ እንደነበርና አሁን ግን በማረሚያ ቤቶች ዉስጥ መረጋጋት መፈጠሩን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ረዳት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አዲሱ ጴጥሮስ ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡ አቶ አዲሱ በጠቅላይ አቃቤ ህግ የምህረት አዋጁ ዝርዝር አፈፃፀም መሰረት በምህረቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ እና ተጠቃሚ የማይሆኑ ታራሚዎች በግልፅ ይፋ ከሆነ በኋላ […]

በሰኔ 16ቱ የቦንብ ፍንዳታ በተጠረጠሩት ላይ የመጨረሻ የምርመራ የሶስት ቀን ተጨማሪ ጊዜ ተሰጠ::

የቀድሞው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ በሰኔ 16ቱ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ከተከሰተው የቦንብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ የስራ ክፍተት አሳይተዋል ተብለው በተጠረጠሩት ላይ 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ተጠይቆ የመጨረሻ የሶስት ቀን ጊዜ ብቻ ተፈቅዷል።

የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ጉዳይ ላይ መክሯል፡፡

ኤርትራ ከኢትዮጵያ ለቀረበላት የእርቅ ጥያቄ የሰጠቸው አወንታዊ ምላሽ ለሰላም ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ነው የተባለው፡፡ ታዲያ ለዚህ የሰላም አጋዥነቷ የተጣለባት ማእቀብ እንዲነሳላት ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግስታ ድርጅት ጥያቄ አቅርባ ነበር፡፡ ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበው አሁን ላይ ድርጅቱ የኤርትራ ማእቀብ ይነሳ ወይም አይነሳ በሚለው ሀሳብ ዙሪያ ምክክር አድርጓል፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስዊድን አምባሳደር ኦልፍ ስኩግ እንዳሉት ኤርትራና […]

ማንነታቸው ያልታወቀ 40 የታጠቁ ወታደሮችን ይዞ ትግራይ ክልል የገባ አንቶኖቭ አውሮፕላን በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዘ።

ማንነታቸው ያልታወቀ 40 የታጠቁ ወታደሮችን ይዞ ትግራይ ክልል የገባ አንቶኖቭ አውሮፕላን በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዘ። ምንጮች ለቢቢሲ እንደገለፁት በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት የታጠቁ ወታደሮች ተልዕኮና ማንነታቸው ባይታወቅም ኢትዮጵያዊያን እንደሆኑ ታዉቋል። ከሁለት ቀናት በፊት ከሱዳን በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ የተጠረጠረው አንቶኖቭ አውሮፕላንና አሳፍሯቸው የነበሩት 40 የታጠቁ ወታደሮች በመቀሌው የአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ መያዛቸውን […]