loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በወርቅ ሜዳልያ ከተመረቁ 400 ተማሪዎች ጋር ተገናኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በወርቅ ሜዳልያ ከተመረቁ 400 ተማሪዎች ጋር ተገናኙ፡፡ ተመራቂዎቹንም አበረታትተዋል፡፡ የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ተማሪዎቹም ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያላቸውን ክብር፣ ፍቅር እና አጋርነት ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቡናን በአለም ገበያ ላስተዋዉቅ ነዉ አለ

” አለም አቀፍ የቡና ቀን በምድረ ቀደምት” በሚል ቡናን ለማስተዋወቅ የመክፈቻ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡ በአየር መንገዱ የኮርፖሬ ት ኮሙኒኬሽን ኦፊሰር አቶ አደፍርስ ታዬ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት በፕሮግራሙ የአየር መንገዱ ሰራተኞች፣የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን እና በቱሪዝም ዘርፍ የሚሰሩ ተቋማት በመገኘት የኢትጵያን ቡና በአለም ገበያ ማስተዋወቅን በተመለከተ ይመክራሉ ፡፡

ዛሬ ኢትዮ ቴሌኮምን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለመምራት ኃላፊነታቸውን የተረከቡትን ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩን እናስተዋውቃችሁ

ዛሬ ኢትዮ ቴሌኮምን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለመምራት ኃላፊነታቸውን የተረከቡትን ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩን እናስተዋውቃችሁ፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢንፎርሜሽን ሲስተም በመጀመርያ ዲግሪ ተመርቀዋል፣ እንግሊዝ ከሚገኘው ኦፕን ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ አዲሷ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በቴሌኮም ዘርፍ ለስምንት ዓመታት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂውን ከመምራት አንስቶ፣ እስከ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነት ድረስ ማገልገላቸውን ከኢትዮ ቴሌኮም ሕዝብ ግንኙነት ክፍል […]

ማይክ ፖምፒዮ የኢራንን መሪዎች ከማፊያ ጋር አመሳስለዋቸዋል

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፒዮ የኢራን መሪዎች ከመንግስትነት ይልቅ የማፊያ ባህርይ ጎልቶ ይንጸባረቅባቸዋል ብለዋል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው ፖምፒዮ ለዚህ አባባላቸው በሀገሪቱ ያለውን ሰፊ ሀብትና የመሪዎቹን በሙስና መዘፈቅ በማሳያነት አቅርበዋል፡፡ ፖምፒዮ ካሊፎርኒያ ውስጥ ባደረጉት ቅስቀሳ የሚመስል ንግግር ኢራናውያን የሀገራቸውን ዕጣ ፈንታ ራሳቸው መወሰን አለባቸው፤ እኛ አሜሪካውያንም ከጎናቸው እንቆማለን ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በየፊናቸው አንዱ […]

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ምክንያት ከስራ የተባረሩ 42 መምህራንን ወደ ስራ እንዲመለሱ ውሳኔ አስተላለፉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከ50 የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተዉጣጡ 3 ሺ 175 መምህራን ጋር እየተወያዩ ነው፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ እውቀት እና የአካዳሚክ ነጻነት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ለሚኖር ነጻ አስተሳሰብ ቅድመ ሁኔታዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። ዶክተር አብይ ለመምህራኖቹ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ በትምህርቱ ዘርፍ የተያዘውን ግብ ለማሳካትም ብቁ መምህራን እና ጥራት ያለው ትምህርት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። ብቃት […]

በአለም አቀፍ ደረጃ የሚሰሩ ሆቴሎች ባህልን የሚያንፀባርቅ ገፅታ ሊኖራቸዉ ይገባል ተባለ

ይህ የተባለዉ የካፒታል ኢንተርናሽናል ሆቴል የባህል አዳራሹን ሲያስመርቅ ነው፡፡ በካፒታል ሆቴል የባህል አደራሽ ምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የከተማዋ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ምክትል ከንቲባ ዳግማዊት ሞገስ የተገኙ ሲሆን ምክትል ከንቲባዋ ዳግማዊትም ከተማችን አዲስ አበባ ብዙ ባህል አዳራሾች ያስፈልጓታል ፤በባህል ላይ የሚሰሩ ባለሀብቶችንም እናበረታታለን ብለዋል፡፡ የካፒታል ሆቴል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አዲስአለም ገብሬ በሆቴላቸዉ ዉስጥ ልዩ […]

የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና እስከ ሐምሌ 25 ባለዉ ግዜ ዉስጥ ይፋ ይሆናል

የሐገር አቀፍ ትምህርት ፈተናዎች እና ምዘና ኤጀንሲ በስሜ በሀሰት የተከፈቱ የተለያዩ የፌስ ቡክ ፔጆች የ12ኛ ክፍል ፈተና ወጥቷል፡፡ በሚል ያስወሩት ወሬ ሀሰት ነዉ ብሏል፡፡ ኤጀንሲዉ አስከ ሀምሌ 25 ግን የፈተናዉ ዉጤት ይፋ እንደሚሆን ለአርትስ ቲቪ ተናግሯል፡፡ በኤጀንሲዉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሾና ለጣቢያችን ፈተናዉ ገና በእርማት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የሀገር አቀፍ ትምህርት […]