loading
15 ሺህ ከስደት ተመላሾችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተገለጸ

15 ሺህ ከስደት ተመላሾችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተገለጸ

አርትስ 27/03/2011

 ይህ የተገለፀው የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እና ከአውሮፓ ህብረት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው መድረክ ላይ ነው ፡፡

በመድረኩ የኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን የቴክኒክ ዋና አማካሪ አይዳ አወል  በ2015 በአምስት ሚሊየን ዩሮ በተጀመረ ፕሮጀክት በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በትግራይ ክልሎች 15 ሺህ ከስደት ተመላሾችን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችሉ የተለያዩ የክህሎት እና የፋይናንስ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።

ፋና እንደዘገበዉ እንደ አይዳ አወል ማብራሪያ በዚህ ፕሮጀክት ትግበራ በ21 ወረዳዎች 60 ሚሊየን ብር ብድር እንዳገኙ ጠቁመዋል፡፡

1 ሺ 500 የሚሆኑት ከስደት ተመላሾችን ደግሞ በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት በማደራጀት 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ብድር እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *