loading
ፖል ካጋሜ በአፍሪካ የመጀመሪያዉን አለም አቀፍ ኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓት ይፋ አደረጉ

አርትስ 23/02/2011

 

ዘ ኒዉ ታይምስ እንደዘገበዉ የሩዋንዳዉ ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ ከቻይናዉ አሊባባ ግሩፕ ጋር በመተባበር ነዉ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነዉን የአለም የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርአት ይፋ ያደረጉት፡፡

ሩዋንዳ  ከአሊባባ ግሩፕ ጋር የግብይይት ስርአቱን ይፋ ባደረጉበት ወቅት የኤሌክትሪክ ግብይይቱን ተግባራዊ ለማድረግ 3 ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቶቹ የተፈረሙት የሃገሪቱን ኢኮኖሚ በመደገፍ የድምበር ተሸጋሪ ንግድን በማዘመንና ለቻይና ተገልጋዮች ምርቶችን ማቅረብ እንዲሁም የሩዋንዳን ቱሪዝም ምቹና ተደራሽ ለማድረግ ነዉ ተብሏል፡፡

የአሊባባ ግሩፕ መስራቹ ጃክ ማ በስምምነቱ  ወቅት እንደተናገሩት፤ ይህ ቀን ሩዋንዳዉያን ምርታቸዉን እና እደጥበባቸዉን የትም ሳይሄዱ ባሉበት ከቻይናና ከአለም ሃገራት ጋር ተገናኝተዉ የሚገበያዩበት በመሆኑ ቀኑን ታሪካዊ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

አሊባባ ግሩፕ የአለማችን ግዙፍ በኢንተርኔት አማካኝነት የሚያገበያይ ተቋም ነዉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *