loading
ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ጁባ ገቡ

አርትስ 21/02/2011

ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባለፈው መስከረም በአዲስ አበባ የተፈረመውን የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ለማብሰር በተዘጋጀው ስነስርዓትላይ ለመሳተፍ ወደ ጁባ ገቡ።

በጁባ ጆን ጋራንግ አደባባይ በሚካሄደው ስነስርዓት ላይ የደቡብ ሱዳን መንግሥትና ተፋላሚ ኃይሎች ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን የተለያዩ ሀገራትመሪዎችም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዚሁ ሥነ ስርዓት ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የዑጋንዳ፣ ሱዳን፣ ኬንያ እና የሌሎች ሀገራት መሪዎችና ተወካዮች ንግግር ያደርጋሉ።

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ከሆኑ በኋላ ይህ ይፋዊ ጉዟቸው ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *