loading
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አርትስ 04/02/2011
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በቆይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ወደ ተግባር ከተሸጋገረ ጊዜ ጀምሮ እያደገ በመጣው በሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ገልፀዋል።

በንግድና ልዩ ልዩ ትብብሮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያካሂዱም ይጠበቃል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *