ፒ.ኤስ.ጂ የ100 ሺ ዩሮ ቅጣት ተጣለበት
ፒ.ኤስ.ጂ የ100 ሺ ዩሮ ቅጣት ተጣለበት
የፈረንሳዩ ፒ.ኤስ.ጂ ክለብ በወጣት ተጫዋቾች ላይ በፈፀመው የዘረኝነት መረጃ አሰባሰብ የ100.000 ዩሮ መቀጣቱን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡
Mediapart የተሰኘው የፈረንሳይ ድረገፅ እንደዘገበው፤ የፈረንሳዩ ክለብ ተጫዋቾችን በሚያስፈርምበት ጊዜ የመጡበትን ዘር የሚገልፅ መረጃ እንደሚይዙ የሚያሳይ መረጃ ይዞ በመውጣት ይፋ አድርጓል፡፡
ይህ ድርጊት ማለትም የአንድን ግለሰብ ዘር እና የመጣበትን ብሄር የሚጠቁም መረጃ መያዝ የፈረንሳይን ህግን የሚፃረር በመሆኑ ክለቡ እየተወቀሰ ይገኛል፡፡
የፈረንሳይ ሊግ (LFP) የስነ ምግባር ኮሚሽን፤ አከራካሪ ቅጣቱን በክለቡ ላይ ሲያሳርፍ ፒ.ኤስ.ጂ እነዚህን መረጃዎች ለልዩነት መፍጠሪያ ዓላማ መጠቀም እንደሌለበት አሳስቧል፡፡
LFP እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከ2013 እስከ 2018 በነበሩ የክለቡ የቀድሞ መልማይ ባለስልጣናቱን ሀሳብ ካደመጠ በኋላ ነው፡፡
መልማዮቹ ለሊግ አንዱ ሻምፒዮን ቡድን እያንዳንዳቸውን ተጫዋቾች በሚመለምሉበት ወቅት ባልተገባ መንገድ ጥያቄዎችን እንደሚያነሱ እና በኤሌክትሮኒክስ መመዝገቢያ የመጡበትን ዘር የሚጠቁም አራት ዝርዝሮች ውስጥ አንዱን እንዲመርጡ ይደረጋል፡፡ እነዚህም ፈረንሳያዊ፣ ሰሜን አሜሪካዊ፣ ጥቁር አፍሪካዊ አሊያም ምዕራብ ህንድ አማራጮች በመሆን ይቀርብላቸዋል፡፡
ክለቡ በህዳር ወር በMediapart ይፋ ለሆነው መረጃ እውነታነት ማረጋገጫ በመስጠት ድርጊቱን እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡