loading
ፍርድ ቤቱ የአቶ አብዲ መሃመድ (አብዲ ኢሌን) የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገ፡፡

ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሀመድ ዑመር ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሰጠ።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት ነው አቶ አብዲ መሀመድ ዑመርን ጨምሮ 3 ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ነው ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ የፈቀደው።
በዚህም መሰረት የፖሊስን የምርመራ ውጤት ለመስማት ለመስከረም 4 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ኤፍ ቢ ሲ

አርትስ 24/12/2010

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *