loading
ፈረንሳይ የቀድሞውን የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ወንድም አሳልፋ ልትሰጥ ነው

ፈረንሳይ የቀድሞውን የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ወንድም አሳልፋ ልትሰጥ ነው

አርትስ 27/03/2011

 ቡርኪናፋሶን ለ27 ዓመት የገዙት የቀድሞው የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ብሌዝ ኮምፓወሬ እና ወንድማቸው ከሰሩት ወንጀል ለመሸሽ በስደት ላይ ይገኛሉ፡፡

የፕዝዳንቱ ወንድም ፍራንሶይስ ኮምፓወሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1998 ኖርበርት ዞንጎ የተባለ የምርመራ ጋዜጠኛ ገድለዋል ተብለው ይጠረጠራሉ፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው ፈረንሳይ ሰውየውን  ለቡርኪናፋሶ መንግስት አሳልፋ ለመስጠት መወሰኗን የፈረንሳይ ይገባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡

በቻርለስ ደጎል አወሮፕላን ማረፊያ በፈረንሳይ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር የዋሉት ፍራንሶይስ ኮምፓወሬ ወንድማቸው ቡርኪናፋሶን ሲመሩ እሳቸው ደግሞ የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ያገለግሉ ነበር፡፡

ጠበቃቸው ፒየር ኦሊቨር ደንበኛቸው ተላልፈው የሚሰጡበት ሂደት ፖለቲካዊ ተነሳሽነት አለው ሲሉ ይከራከራሉ፡፡

ለዚህ አባባላቸው የሚጠቅሱት ምሳሌ ደግሞ የቀድሞው ፕሬዝዳንትና የተከሳሹ ወንድም ብሌዝ ኮምፓወሬን  ኮትዲቯር አሳልፌ አልሰጥም ስትል ዝም መባሉን ነው፡፡

ብሌዝ ኮምፓወሬ ወደ ኮትዲቯር የተሰደዱት ከሳቸው በፊት የነበሩትን የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ቶማስ ሳንካራን ገድለዋል ተብለው በወንጀል ስለሚፈለጉ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *