loading
ጦርነቱ ህዝባዊ ይደረግ ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 10፣2013 የአማራ ክልል ህዝብ ጦርነቱን ህዝባዊ እንዲያደርገው ርዕሰ መስተዳደር ጥሪ አቀረቡ:: የህወሓት የሽብር ቡድን ጦርነቱን ህዝባዊ ስላደረገው የአማራ ክልል ህዝብም በተመሳሳይ መንገድ ጦርነቱን ህዝባዊ እንዲያደርገው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር ጥሪ አቀርበዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳደሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የህወሓት የሽብር ቡድን በዋናነት በሶስት ግንባሮች ማለትም በሰሜን እና በደቡብ ጎንደር እንዲሁም በሰሜን ወሎ ወረራ መፈፀሙን ገልፀዋል፡፡ በዚህም በየደረሰበት ሴቶችን ደፍሯል፣ የግለሰብና የመንግስት ንብረቶችን ዘርፏል፤ ወጣቶችንም አፍኖ ወስዷል ብለዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ በወረራቸው አካባቢዎች የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ እና የተለያዩ ክልሎች ልዩ ኃይሎች፣ የአማራ ሚሊሻና ፋኖዎች ቡድኑን ለመደምሰስ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዚህም በሽብር ቡድኑ ላይ ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ መድረሱን አቶ አገኘሁ ተናግረዋል፡፡
በተያያዘም ህዝቡ በቀረበለት የክተት ጥሪ የሰጠው ምላሽ የሚያኮራ ነው ሲሉ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለፁ::ህዝቡ በቀረበለት የክተት ጥሪ የሰጠው ምላሽ የሚያኮራ እንደሆነ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡

ለህልውና ዘመቻው ከመደበኛ ሠራዊት በተጨማሪ ወጣቶች፣ ፋኖዎች፣ ተመላሽ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና መላው የአማራ ሕዝብ እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ላደረጉትና እያደረጉ ላሉት ልዩ ልዩ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *