loading
ጥይት ያለአግባብ አታባክኑ-ዶክተር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 ሁሉም ለቀጣይ ትግል በሚዘጋጅበት ወቅት ጥይት ያለ አግባብ ማባከን አይገባም ሲሉ የአማራ ክልል
ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ አሳሰቡ፡፡ርዕሰ መስተዳድሩ በሰጡት መግለጫ ከአሸባሪው የትሕነግ ወራሪ ቡድን ጋር በተካሄደው ፍልሚያ
በጀግንነት ተጋድሎ ያደረጉ የጸጥታ አካላት ለከፈሉት መስዋእትነት ትልቅ ክብር አለን ብለዋል።


በግንባር ለተፋለሙ ጀግኖች አቀባበል ማድረግ ተገቢ ቢሆንም ለአቀባበል በሚል የጥይት ተኩስ
ማድረግ ማኅበረሰቡን ረብሿል፤ የክልሉ መንግሥትም በዚህ ደስተኛ አይደለም ነው ያሉት።
ጦርነቱ ገና አለማለቁን እና ትግሉ ቀጣይ መሆኑን በመግለጽ ጠላት ነገ ተመልሶ እንዳይወረን በጀግንነት
እና በኃላፊነት መንፈስ ለመዋጋት ሁሉም መዘጋጀት ባለበት ወቅት ጥይትን ያለ አግባብ ማባከን
ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው ብለዋል፡፡


ጦርነቱ ሳይጠናቀቅ ጥይትን ማባከን የአገሪቱንም ይሁን የክልሉን ምጣኔ ሃብት ስለሚያዳክም
በየትኛውም አካባቢ የሚመለስ ኃይል ጥይት መተኮስ እንዲያቆም አሳስበዋል።
የመጨረሻው ድል እስኪገኝ ጦርነቱ እንደሚቀጥል የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ከድል ማግስት የጸጥታ
ኃይሉ በሰራው ተጋድሎ ልክ እውቅና እንሰጣለን፤ ለመጪው ትውልድም እንዲታወስ እናደርጋለን
ማለታቸውን ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *