loading
ጠ/ሚ አብይ በግድቡ ላይ ባሉ አለመግባባቶችና የውይይት መጓተቶች ላይ ስብስባ እንዲጠራ ጠየቁ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2013 ጠ/ሚ አብይ በግድቡ ላይ ባሉ አለመግባባቶችና የውይይት መጓተቶች ላይ ስብስባ እንዲጠራ ጠየቁ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ ለጻፉት ደብዳቤ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፥ ኢትዮጵያም የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበርና ለዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ ከግድቡ ጋር በተያያዘ ባሉ መጓተቶች ላይ ስብሰባ እንዲጠሪ ሃሳብ አቅርባለች፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እስካሁን በግድቡ ዙሪያ የተካሄደው ውይይት እንዳልተሳካ መቁጠር አግባብ አለመሆኑን ጠቅሰው፥ ለዚህም እንደ የመርሆዎች ስምምነት መፈረም እና የብሔራዊ ገለልተኛ የሳይንስ ምርምር ቡድን መመስረትን በመልካም ማሳያነት አንስተዋል፡፡ በግድቡ ዙሪያ የሚደረጉ ድርድሮች ህጋዊና ቴክኒካዊ ተግዳሮቶች ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርጉ ስምምነቶች ላይ ለመድረስ እንቅፋት መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ለዘጠኝ ጊዜያት ያህል መስተጓጎል የገጠመውን የሦስትዮሽ ድርድር ዕውን እንዲሆን ያደረገው ጥረት አድነቆታቸውን ገልጸዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ በሕዳሴ ግድብ ላይ የሚካሄደው የሦስትዮሹ ድርድር አሁንም ቢሆን በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር እንዲቀጥል ጽኑ ፍላጎትት እንዳላት በደብዳቤያቸው ገልጸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *