loading
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕገ-ወጦችን ሕግ ፊት የማቅረቡ ሥራ ህዝቡን በማስደሰቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል አለ

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕገ-ወጦችን ሕግ ፊት የማቅረቡ ሥራ ህዝቡን በማስደሰቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል አለ

አርትስ 25/03/2011

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለአርትስ በላከው መረጃ ሀገሪቱ የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ ዳር ለማድረስ እና የፍትህ ሥርዓቱን አሰራር ውጤታማ፤ ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ በትጋት እየሰራ መሆኑን አስታውሶ እርምጃው ህዝቡን በማስደሰቱ በፍትህ ስርአቱ ከህግ ውጭ የሆኑ ተግባራትን በማደን ተጠያቂ አካላትን ህግ ፊት እያቀረበ መሆኑን ገልጧል፡፡

በቀጣይም በተደራጁ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ ሙስናና ሌብነት ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲሁም ሌሎች ላይ የተሳተፉ ሕገ-ወጦችን ወደ ሕግ የማቅረቡ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል፡፡

መንግስት ይህንን አካሔድ ተከትሎ ከሕግ ውጭ የሆኑ አካላትን ለሚፈጽሙት ተግባር የማይታገስና ለድርድር የማያቀርብ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ግጭቶችን በቀሰቀሱ እና ለበርካታ ህይወት መጥፋትና ጉዳት ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ምርመራ በማድረግ የሕግ የበላይነትንና የሕዝቡን ደህንነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን አስገንዝቦ የተገኙ ዉጤቶችን ለሕዝቡ የማሳውቅ ይሆናል ብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *