loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጀርመን በርሊን ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጀርመን በርሊን ገቡ

አርትስ 20/02/2011

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የፈረንሳይ ጉብኝታቸወን አጠነቀው ጀርመን በርሊን ገብተዋል፡፡

በጀርመን ቆይታቸው ከጀርመን መረሂተ መንግስት አንጌላ መርክል ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ፡፡

ከሁለትዮሽ ውይይቱ ባሻገር የቡድን 20 አባል አገራት የአፍሪካን ልማት ለማገዝ በመሰረቱት ኮምፓክት አፍሪካ በሚሰኘው ጉባኤ ላይ ይገኛሉ፡፡ በቡድን 20 አገራት የተመሰረተውና በጀርመን አነሳሽነትተግባሩን እየከወነ ያለው ኮምፓክት አፍሪካ ለአፍሪካ ልማት የተሻሉ አማራጮችን በመቅረብ ትብብር የማድረግ ስራ የሚሰራ ነው፡፡

እስከ አሁን ከ7 ያላነሱ የአፍሪካ አገራት ተጠቃሚ እየሆኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያም ከእነዚሀ ውስጥ አንዷ ናት፡፡ በመሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ መድረክ ተገኝተው በውይይቱ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

በመቀጠልም ወደ ፍራንክፈርት በማቅናት “አንድ ሆነን እንስራ ነገን እንገንባ” በሚል መሪ ቃል ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር የሚገናኙ ይሆናል፡፡

ኢ ቢ ሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *