loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በቀጠናው ለሚያከናውኑት ተግባር ኬንያ ድጋፍ ታደርጋለች አሉ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፡፡

ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ ፈጣን እርምጃዎችን እየሰወደ ይገኛል።
እየተወሰደ ካለው እርምጃም የሀገሪቱን አንድነት ለማጠናከርና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት እንዲሁም ከኤርትራ ጋር ሰላምን ለማስፈን እየተከናወኑ ያሉትን ተግባራት በአብነት አንስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሁን እያከናወኑት ላለው ተግባር ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ያሉት ፕሬዚዳንት ኡሁሩ፥ ለዚህ ደግሞ ኬንያ ሙሉ ትብብር እንደምታደርግላቸው ቃል ገብቼላቸዋለሁም ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አክለውም፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለምስራቅ አፍሪካ ቀጠና በሙሉ በጎ አመለካከት አላቸው ብለዋል።
በቀጠናው ሰላም እና መረጋጋትን በማምጣት እየሰራ ላለው የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስተዳደር ኬንያ ከጎኑ ትቆማለች ሲሉም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ሁኔታ ደስተኞች ነን ያሉት ፕሬዚዳንት ኡሁሩ፥ ከኤርትራ ጋር በተደረሰው ስምምነትም ተደስቻለሁ ብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት እስካሁን የተከናወኑ ስራዎች ድምርም ለቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት ጠቀሜታ እንዳለውም ተናግረዋል።
በጦርነትና በግጭት የሚታወቀው ቀጠና ወደ ሰላምና መረጋጋት መምጣቱ ዋጋው ከጸጥታ ባሻገር ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ኡሁሩ፥ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ራዕይ ምስራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ዜጎችን መጥቀም ያስችላል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀጠናው ትልቅ ራዕይ አላቸው ያሉት ፕሬዚዳንት ኡሁሩ፥ ይህ ራዕይ እንዲሳካ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በቅርበት ለመስራት እቅድ አለኝም ብለዋል።
ኤፍ ቢ ሲ

አርትስ 24/12/2010

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *