loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ ኤል ሲሲ ጋር ተወያዩ

አርትስ 27/12/2010
ለቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም ቤጂንግ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ ኤል ሲሲ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

መሪዎቹ የተለያዩ የሁለትዮሽ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳች ላይ መክረዋል።

በውይይታቸው ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብም አንዱ የተወያዩባቸው ጉዳይ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጉባኤው በተዳኝ የተለያዩ የሁለትዮሽ ውይይቶችን በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ትናንት የሩዋንዳውን ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜን አግኝተው አነጋግረዋል።

ዛሬም ከቻይና ኤግዚም ባንክ ሊቀመንበር ሁ ዢያኦሊያን ጋር በቤጂንግ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በባንኩ መካከል ባለው ትብብር ዙሪያ መክረዋል።

በተለይም መዳረሻቸውን ኢትዮጵያ ያደረጉ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቶችን ማሳደግ በሚችሉበት ዙሪያ ተወያይተዋል።

ሊቀመንበሯ ኢትዮጵያ እየወሰደች ያለቻቸውን የኢኮኖሚ መሻሻያዎች አድንቀዋል።

ኤፍ ቢ ሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *