loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በገበታ ለሀገር እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ።

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በገበታ ለሀገር እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ የዛሬ ዓመት ቃል የገባነውን ፈጽመን በተግባር አሳይተናል ብለዋል። በገበታ ለሀገር ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የገንዘብ መጠን እንዲያዋጡ የተዘጋጀውን የባንክ ሂሳብም ይፋ አድርገዋል፡፡

በዚህም የ10 ሚሊየን እና የ5 ሚሊየን ብር ገቢ ለማድረግ እንዲሁም ከሀገር ውስጥ ማንኛውም መጠን ያለውን ገንዘብ አስተዋጽዖ ለማድረግ የባንክ ሂሳብ ቁጥር፦ 1000339911267 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ እንዲጠቀሙም ጠይቀዋል።እንዲሁም ከሃገር ውጭ ለሚገኙ ወገኖች በ0100101300591 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መጠቀም ይችላሉ፡፡በተጨማሪም መላው ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን ያህል የገንዘብ መጠን ለማዋጣት ወደ 333 አጭር የጽሑፍ መልዕክት በመላክ አሻራቸውን እንዲያሳርፉም ጥሪ አቅርበዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *