loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 03፣ 2014  በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራ ልዑክ በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳ ጎብኝቷል። በጉብኝቱም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም ከፍተኛ
የፌደራልና የክልል የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጉብኝቱ ላይ ፥ ከዚህ በፊት የማይታረሱ መሬቶችን በማረስ በኩታ ገጠም እርሻ በስንዴ ምርት እራሳችንን ለመቻል ሰፊ ስራዎችን እየሰራን ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም የግብርና ልማታችን የእድገታችን መሰረት ስለሆነ ልዩ ትኩረት በመስጠት ይሰራል ያሉ ሲሆን፥ በግብዓትና በገበያ ትስስር ውጤታማ እንዲሆን ይደረጋል ብለዋል። የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመለስ አብዲሳ ፥ ዘንድሮ በክልሉ ከሚመረተው የስንዴ ምርት ውስጥ 74 በመቶ በኩታ ገጠም የሚመረት ነው ብለዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *