loading
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ጨምሮ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች ጉብኝታቸውን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጀመሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ጨምሮ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች ጉብኝታቸውን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጀመሩ

አርትስ 30/02/2011
መሪዎቹ በአማራ ክልል ለሚያደርጉት ጉብኝት ዛሬ ጎንደር ከተማ ሲገቡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በቆይታቸውም ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አሁን ላይ መሪዎቹ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት እያደረጉ ነው።
የጎንደር ቆይታቸውን ሲያጠናቅቁ በባህር ዳር ከተማ ጉብኝት እንደሚያደርጉም ነው የሚጠበቀው።
የመሪዎቹ ጉብኝት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሁለቱ መሪዎች አማራ ክልልን እንዲጎብኙ በይፋ መጋበዛቸውን ተከትሎ ነው።
ግብዣው በአፍሪካ ቀንድ ሰላም ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ የሚገኘውን የለውጥ እንቅስቃሴና የኢኮኖሚ ትብብርን ለማመቻቸት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የሚያካሂዱት እንቅስቃሴ አካል ነው ተብሏል።
ባለፈው ወር በአስመራ የተካሄደው የሶስትዮሽ ምክክር ተከታይ የሆነው ጉብኝት ውይይቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያለመ ሲሆን፥ በጎንደርና ባህር ዳር የሚገኙ የልማት እንቅስቃሴዎችን ጉብኝትም ያካትታል ብሏል የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት፡፡
ፎቶ ኤፍ ቢ ሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *