loading
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ችግር ለመፍታት በተደረገዉ ጥረት የሀገር ሽማግሌዎች ሊመሰገኑ ይገባል አሉ፡፡  

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ችግር ለመፍታት በተደረገዉ ጥረት የሀገር ሽማግሌዎች ሊመሰገኑ ይገባል አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ለሶዴፓ ጉባኤተኞች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለክልሉ ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል::

በመልዕክታቸውም ባለፈው አመት ወደ ሀላፊነት ከመጡ በኋላ መጀመሪያ የተንቀሳቀሱት ወደ ሶማሌ ብሄራዊ ክልል መሆኑን አስታውሰው ባለፈው አመት ወደ ክልሉ የመጡት በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ችግር ለመፍታት እንዲቻል ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ለመወያየት የነበረ መሆኑን አስታውሰዋል::

ችግሮቹንም መፍታት በመቻላቸው ምስጋናም አቅርበዋል፤በንግግራቸውም በተፈጠረው ሰላምም የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር አባላት እና አመራሮች እንዲሁም በእስር ቤቶች ሲማቅቁ የነበሩ ወገኖች ታዳሚዎች መሆናቸው ልዩ ትርጉም ያለው የለውጥ ውጤት መሆኑን አውስተዋል::

በለውጡ ሄደትም በሶማሌ ክልል አየር ላይ አዲስ የሰላም አየር መንፈሱን ለሶማሌ ክልል እና ለሀገራችን ትልቅ የለውጥ ስኬት መሆኑን አንስተዋል::

የሶማሌ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ በተሟላ ሁኔታ በምሁራን እንዲመራ መደረጉ መልካም ጅምር መሆኑን እና ፓርቲውም የሶማሌ ዴሞክራቲክ ፓርቲ /ሶዴፓ/ በማለት መቀየሩ የሶማሌ ህዝብ ያለምንም ተቀፅላ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ያረጋገጠ መሆኑን አንስተዋል::

የክልሉ አመራር እና ህዝብ ቀጣዩ ስራ መስኖን ማስፋፋት፣ የስራ አጥነትን ችግር ለመፍታት ጠንክሮ መስራት፣ ኮንትሮባንድን፣ የፖለቲካ እና የገንዘብ ሌቦችን መታገል መሆኑን አመላክተዋል:: ክልሉ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ የኢፌድሪ መንግስት ድጋፍ የማይለየው መሆኑን አረጋግጠዋል::

በመጨረሻም፣ የዛሬ አመት የክልሉ ሽማግሌዎች በሶማሊላንድ አስተዳደርና በሶማሊያ መንግስት መካከል መግባባት እንዲኖር ዶክተር አብይ  የበኩላቸዉን እንዲያደርጉ ጥሪ ባቀረቡላቸዉ መሠረት፣ በለፉት ወራት ከሁለቱም መሪዎች ጋር ተገናኝተዉ በመደመር ፍልስፍና አብርዉ ለመስራት ማስማማታቸውን አስታዉሰዋል።

የሁለቱም ወገኖች መስማማትም ለቀጠናዉ ዉህደት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *