loading
ጋቦን በዓሊ ቦንጎ ላይ የተቃጣውን መፈንቅለ መንግስት  አከሸፍኩ አለች

ጋቦን በዓሊ ቦንጎ ላይ የተቃጣውን መፈንቅለ መንግስት  አከሸፍኩ አለች

በቤተሰብ መወራረስ ለ50 ዓመታት ፀንቶ የነበረው የፕሬዝዳንት ዓሊ ቦንጎ ዙፋን እሳቸው በሌሉበት ሊገለበጥ ተቃርቦ እንደነበር ታማኞቻቸው ተናግረዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው የፕሬዝዳንቱ የፀጥታ ሰዎች የመፈንቅለ መንግስቱን ሴራ ያቀነባበሩትን ሁለት ተጠርጣሪዎች ሲገድሉ ሌሎች ሰባት ተባባሪዎችን ደግሞ በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል፡፡

የጋቦን መንግስት ቃል አቀባይ ቤርትራንድ ማፓንጉ በመግለጫቸው እደተናገሩት ጥቂት ወታደሮች አንድ የሬዲዮ ጣቢያን ለአጭር ጊዜ ተቆጣጥረው ነበር፡፡

ሬዲዮ ጣቢያውን በተቆጣጠሩበት ወቅትም  ፕሬዝዳንት ቦንጎ ከእንግዲህ ሀገር ለመምራት የሚያስችል አቅም የላቸውም የሚል መልእክትም ለህዝቡ አስተላልፈዋል፡፡

የመፈንቅለ መንግሰቱን ሙከራ ያደረጉት የአርበኞች ንቀናቄ በሚል ቡድን የተደራጁ የመከላከያ እና የደህንነት አባላት ናቸው፡፡

ይህን ዜና የሰሙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋቦናዊያን በሬዲዮ ጣቢያው አቅራቢያ በመገኘት ለመፈንቅለ መንግስቱ ድጋፋቸውን ሲገልፁ በፍጥነት በፕሬዝዳንቱ ታማኝ ወታደሮች ተበትነዋል ነው የተባለው፡፡

የ59 ዓመቱ ቦንጎ ባጋጣማቸው በአንጎል ውስጥ የደም መፍሰስ ህመም ከህዳር ወር ጀምሮ ለህክምና ከሃገራቸው እንደወጡ አልተመለሱም፡፡

ሞሮኮ በህክምና የሚገኙት ፕሬዝዳንቱ ከሳምንት በፊት በቴሌቭዥን ቀርበው ደህና ነኝ ቢሉም ቀኝ እጃቸው መንቀሳቀስ እንደማይችል ተነግሯል፤ አንዳንዶቹ መራመድ ስለመቻላቸውም ጥርጣሬ አላቸው፡፡

አሁን ላይ በሀገሪቱ የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ በዋና ከተማዋ ሊብሪቪሌ የሰዓት እላፊ አዋጅ ተጥሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *