loading
ጅማ አባ ጅፋር ወደ ተከታዩ ማጣሪያ አልፏል

ጅማ አባ ጅፋር ወደ ተከታዩ ማጣሪያ አልፏል

አርትስ ስፖርት 25/03/2011

በ2018/19 የቶታል ካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ በመጀመሪያ ጨዋታ የ3 ለ 1 ድል ይዞ የተመለሰው ጅማ አባ ጅፋር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲየም የመልሱን ጨዋታ ከጅቡቲው AS Ali Sabieh or ASAS Djibouti Télécom/ አሳስ ጅቡቲ ቴሌኮም ጋር  በአዲስ አበባ ስታዲየም ተጫውቶ በ2 ለ 2 ውጤት ተለያይቷል፡፡ የአቻነት ግቦቹን ለጅማ አባ ጅፋር ማማዱ ሲዲቤና ዲዲዬ ለብሪ ሲያስቆጥሩ ለእንግዳው ጅቡቲ ቴሌኮም መሀዲ ሁሴን እና ፋታኢ አቢዶን ኳስን ከመረብ አገናኝተዋል፡፡

የጅማው ቡድን በአጠቃላይ ውጤት 5 ለ 3 ተከታዩን ማጣሪያ ተቀላቅሏል፡፡ በማጣሪያው ከግብፁ አል አህሊ ስፖርቲንግ ክለብ ጋር በግብፅ አሌክሳንድሪያ በቦርጅ አል አረብ ስታዲየም ከ10 ቀናት በኋላ በታህሳስ 05/2011 ዓ/ም የሚገናኝ ይሆናል፡፡

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ደግሞ መከላከያ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ በ10: 00 የቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ፡፡

የጦሩ ቡድን ባለፈው ሳምንት ኢኑጉ ላይ ከናይጀሪያው ሬንጀርስ ኢንተርናሽናል ጋር ተጫውቶ የ2 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዶ መመለሱ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *