loading
ጃፓን የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ልትደነግግ ነው::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 26፣ 2013 ጃፓን የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ልትደነግግ ነው:: ጃፓን በሶስተኛው ዙር የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስረጭት አደጋ ውስጥ መሆኗን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዮሺሂንዴ ሱጋ በመግለጫቸው እንዳሉት አሁን ላይ ሀገሪቱ ያጋጠማትን የበሽታውን ስርጭት ስጋት ለመቀነስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመደንገግ እንገደዳለን ብለዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ጃፓን ከ4 ቀናት በፊት በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ4 ሺህ 500 በላይ ታማሚዎችን የያስመዘገቡት ቶኪዮና አካባቢዋ አዋጁ በመንግስት እንዲደነገግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ቀንም ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች በሽታው እንዳለባቸው ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል ከግመሽ በላይ የሚሆኑት ቶኪዮና አጎራባች አውራጃዎች መሆናቸው ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለዚህ ውሳኔ ያነሳሰቸው፡፡

ጃፓን ባለፈው ሚያዚያ ወር የጣለችው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የንግድ ሱቆች እንዲዘጉና ሰዎች በቤታቸው እንዲቆዩ የሚደነግግ ቢሆንም አዋጁን ለሚተላለፉ ቅጣት አላስቀመጠም ነበር፡፡ አሁን ግን የሀገሪቱ ፓርላማ በአስቸኳይ ተሰብስቦ ድንጋጌውን ጥሰው በተገኙ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የቅጣት ህግ እንዲያወጣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሱጋ ግፊት እያደረጉ ነው ተብሏል፡ ጃፓን የኮቪድ-19 ክትባትን ለመጀመር እየተዘጋጀች ሲሆን አዛውንቶችና አረጋዊያንን በመንከባከብ
ስራ ላይ ለተሰማሩ ቅድሚያ ይሰጣል ነው የተባለው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ስራውን ስንጀምር እኔ ራሴ ቀዳሚ ሆኘ ክትባቱን በመውሰድ ህዝቡን ማበረታታት
እፈልጋለሁ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *