“ ጀግኒት ልጆቿን በማስተማር ጾታዊ ጥቃትን ትከላከላለች !” በሚል መሪ ቃል ሲከበር የነበረዉ የዘንድሮ የ16ቱ ቀናት የፀረ – ፆታዊ ጥቃት ንቅናቄ ተጠናቀቀ
“ ጀግኒት ልጆቿን በማስተማር ጾታዊ ጥቃትን ትከላከላለች !” በሚል መሪ ቃል ሲከበር የነበረዉ የዘንድሮ የ16ቱ ቀናት የፀረ – ፆታዊ ጥቃት ንቅናቄ ተጠናቀቀ
አርትስ 02/04/2011
በሴቶች፤ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የሴቶች ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ የሆኑት ወ/ሮ ስመኝ ዉቤ እንደገለፁት “የሴቶችን ጥቃት መከላከል ወይም ማስቆም በ16 ቀናት እቅድ የሚወሰን ወይም በአንድ ቀን ኩነት ብቻ የሚታወስ ሳይሆን እነዚህ 16 ቀናት ጥቃትን ለመከላከልና ለማስቆም ብሎም ለጥቃት ተጎጂዎች አሰፈላጊ ድጋፎችን ለማድረግና በአጠቃላይ የህብረተሰቡንና የወንዶች አጋርነትን የምናጎላበት ንቅናቄ ነዉ ብለዋል”፡፡ በመድረኩ ፆታዊ ጥቃት ደርሶባቸዉ ችግሩን ተቋቁመዉ ለስኬት የበቁ ሴቶች የህይወት ምስክርነታቸዉን ለመድረኩ ተሳታፊዎች አጋርተዋል፡፡ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የበላይ አመራር በኩል የ16ቱ ቀናት የፀረ – ፆታዊ ጥቃት ንቅናቄ መርሀ-ግብር በማስመልከት አበረታች ስራ ለሰሩ ተቋማትና የተሃድሶ ማዕከላት የእዉቅና ሰረተፍኬት ተሰጥቶ በዳግማዊ ምኒሊክ መታሰቢያ ሆስፒታል የሚገኘዉን የአንድ መስኮት አገልግሎት ማዕከል ጉብኝት ተደርጎ የፕሮግራሙ ማጠቃለያ ሆኗል፡፡