loading
ዶክተር አንቶኒ ፋውቺ በአሜሪካ በቅርቡ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ሊባባስ እንደሚችል አስጠነቀቁ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 ዶክተር አንቶኒ ፋውቺ በአሜሪካ በቅርቡ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ሊባባስ እንደሚችል አስጠነቀቁ:: ዶክተር ፋውቺ ይህን አስተያየት የሰጡት አሜሪካዊያን ሰሞኑን ያከበሩትን የምስጋና ቀን በማስታወስ ነው፡፡ ፋውቺ በሰጡት መግለጫ በዓሉን ለማክበር ከቤታቸው ውጭ ጉዞ ያደረጉ አሜሪካዊያን እድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ከሆኑ አዛውንቶችን እንዳይጎበኙ አሳስበዋል፡፡

በዓሉን ለመታደም ከ26 ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን አየር መንገዶችን አጨናንቀው እንደነበር ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል፡፡ይሄ ደግሞ ከ270 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ለሞቱባት አሜሪካ የቫይረሱ ስርጭት ዳግም እንዲባባስ በር ከፋች ነው ተብሏል፡፡ ዶክተር ፋውቺ በሰጡት ማሳሰቢያ አሁንም ቢሆን በዓሉን አክብረው ወደ ቤታቸው የተመለሱ ሰዎች ስርጭቱን ለመቀነስ የሚያስችል ጥንቃቄ ካደረጉ ቢያንስ ሌሎችን ሊታደጉ ይችላለሉ ብለዋል፡፡

እነዚህ ሰዎች ይህን ማድረግ የሚችሉት በሚንቀሳቀሱበት ስፍራ ሁሉ የፊት መሸፈኛ ጭንብሎችን በማድረግና አካላዊ እርቀትን በመጠበቅ ሊሆን እንደሚገባም ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡ አሜሪካ በአሁኑ ጊዜ ከ270 ሺህ በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ የሞቱባት ሲሆን በበሽታው የተያዙት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ13 ሚሊዮን በላይ ተሻግሯል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *