loading
ደቡብ ኮሪያ ከ49 ቀናት በኋላ ትልቁን የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር አስመዘገበች::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012 ደቡብ ኮሪያ ከ49 ቀናት በኋላ ትልቁን የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር አስመዘገበች::የደቡብ ኮሪያ የበሽታዎች መከላከያ   ማእከል ይፋ ባደረገው መረጃ እንዳስታወቀው በሀገሪቱ በአንድ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ስፍራ ነው በርካታ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው የተገኙት፡፡ አልጀዚራ   እንደዘገበው ደቡብ ኮሪያ ክስተቱ ያጋጠማት የቫይረሱን ስርጭት ተቆጣጥሬዋለሁ በማለት ትምህርት ቤቶችን መክፈት በጀመረችበት ወቅት መሆኑ ድንጋጤን   ፈጥሯል፡፡ በዚህ የግብይት ስፍራ በ24 ሰዓታት ስጥ በተደረገ የላቦራቶሪ ምመራ 40 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውተረጋግጧል ነው የተባለው፡፡

የጤና ባለሙያዎች በዚህ የንግድ ማእከል አሁንም ስርጭቱ ከፍ ሊል ስለሚል አሰፈላጊው ክትትል እና ተጨማሪ ምርመራ ያስፈልጋል ሲሉ  አስጠንቅቀዋል፡፡አሁን      ላይ ደቡብ ኮሪያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ዜጎቿ ቁጥር ከ11 ሺህ በላይ የደረሰ ሲሆን ከ260 በላይ

ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይዎታቸው አልፏል፡፡ደቡብ ኮሪያ ቫይረሱን በመከላከሉ ረገድ ከእስያ ሀገራት የተሻለ አፈፃፀም እንዳሳየች ብዙዎች   ይመሰክሩላታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *