loading
ደቡብ ሱዳን ከሶስት ዓመት በኋላ ምርጫ እንደምታደርግ አስታወቀች፡፡

ይህ የገለጸችዉ ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘዉ ኤምባሲዋ ለጋዜጠኞች በሀገሪቱ ስላለው ወቅታዊ የሰላም ሁኔታ ላይ መገለጫ በሰጠችበት ወቅት ነው፡፡
በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጀምስ ሞርጋን እንደገለጹት አሁን ላይ በሀገሪቱ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል ብለዋል፡፡
የሀገሪቱ መንግስት ከተቃዋሚዎች ጋር ስልጣን ለመጋራት ባለፈው ወር ሱዳን ካርቱም ላይ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ ለዚህም የስምንት ወራት የመዘጋጃ ጊዜ ተቀምጧል፡፡
በሀገሪቱ አሁን ላይ ለመጣው ሰላም የዶ/ር አብይ አህመድ አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት አምባሳደሩ ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *