የ8ኛ ዓመት የህዳሴ ዋንጫ ከየካቲት 22 -24/2011 ዓ.ም ይከናወናል፡፡
የ8ኛ ዓመት የህዳሴ ዋንጫ ከየካቲት 22 -24/2011 ዓ.ም ይከናወናል፡፡
የ8ኛ ዓመት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዓመታዊ የእግር ኳስ ውድድር በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሚሳተፉ 4 ክለቦች መካከል የእግር ኳስ ጨዋታ ይካሄዳል ተብሏል፡፡
‹‹የታላቁ ህዳሴ ግድባችን መጠናቀቅ ብሄራዊ ኩራት ነው›› በሚል መሪ ሀሳብ በሚከናወነው በዚህ ውድድር ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሲዳማ ቡና እና አዳማ ከተማ ከየካቲት 22 -24/2011 ዓ.ም ይፎካከራሉ፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለአርትስ በላከው መግለጫ የውድድሩ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት የተካሄደ ሲሆን የካቲት 22 በአዲስ አበባ ስታዲየም 9፡00 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ ቡና፤ በ 11፡00 ሰዓት ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዳማ ከተማ ይጫወታሉ፡፡
የካቲት 24/6/2011 ዓ.ም ደግሞ የሁለቱ ጨዋታ አሸናፊዎች ለዋንጫ፤ ተሸናፊዎቹ ደግሞለደረጃ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡
ውድድሩን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ም/ቤት ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰናድተውታል፡፡