loading
የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ሰርተፍኬት ፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ፣ የልደትና ሞት ሰርተፍኬት እንዲሁም የጋብቻ እና ፍቺ ሰርተፍኬቶች በዲጂታል ሰርተፍኬት ሊቀየሩ ነው፡፡

የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ሰርተፍኬት ፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ፣ የልደትና ሞት ሰርተፍኬት እንዲሁም የጋብቻ እና ፍቺ ሰርተፍኬቶች በዲጂታል ሰርተፍኬት ሊቀየሩ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚስተዋለውን ህገወጥነት እና ሃሰተኛ የመታወቂያ አገልግሎት ለማስቀረት የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪነት መታወቂያን በዲጂታል መታወቂያ እየቀየረ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ከመታወቂያ ስራው በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር Troy Security Solutions group ከተባለ የአሜርካ ኩባንያ ጋር የትምህርት ማስረጃዎችን በተለይም የ8ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፊኬት(ሚኒስትሪ) ፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት(ካርታ) ፣ የልደት ሰርተፍኬት ፣ የሞት ሰርተፍኬት ፣ የጋብቻ ሰርተፍኬት እና የፍቺ ሰርተፍኬቶችን በዘመናዊ ዲጂታል ሰርተፍኬት ለመቀየር ተስማምቷል፡፡
ኢንጀነር ታከለ ኡማ ከድርጅቱ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት “መረጃዎቹን በዲጂታል ሰርተፍኬት መለወጥ የህገወጥ(ፎርጂድ) ማስረጃ አገልግሎትን ከማስቀረቱ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ የሚሰጠውን አገልግሎት ምቹ እና ዘመናዊ ያደርገዋልም” ብለዋል መረጃዉን ያገኘነዉ የከንቲባ ፅህፈት ቤት ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *