loading
የ15ኛ ሳምንት የአንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ይደረጋሉ

የ15ኛ ሳምንት የአንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ይደረጋሉ

አርትስ ስፖርት 25/03/2011

በሳምንቱ አጋማሽ የ15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሲከናወኑ ዛሬ ምሽት አራት ያህል ጨዋታዎች ይደረጋሉ፤ 4፡45 ላይ በቪታሊቲ ስታዲየም በርንማውዝ ሀደርስፊልድ ታውንን ሲያስተናግድ፤ በአሜክስ ብራይተን ኤንድ ሆቭ አልቢዮን ከ ክሪስታል ፓላስ እንዲሁም በለንደን ኦለምፒክ ስታዲየም ዌስት ሃም ዩናይትድ ከ ካርዲፍ ሲቲ ጋር ይጫወታሉ፡፡

የሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ ወደ ቪካሬጅ ሮድ አቅንቶ 5፡ 00 ሰዓት ዋትፎርድን የሚገጥም ይሆናል፡፡ ለፔፕ ጓርዲዮላ ቡድን አጉዌሮና ኬቨን ዲ ብሯይኔ ዛሬ በጉዳት ምክንያት ግልጋሎት እንደማይሰጡ እየተነገረ ይገኛል፡፡

በነገው ዕለት ደግሞ ምሽት 4፡ 45 ሲል በርንሊ ከ ሊቨርፑል፣ ኢቨርተን ከ ኒውካስትል ዩናይትድ፣ ፉልሃም ከ ሌስተር ሲቲ፣ ወልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ ከ ቼልሲ ይጫወታሉ፤ ምሽት 5፡ 00 ላይ የሳምንቱ ተጠበቂ ጨዋታ በማንችስተር ዩናይትድ እና አርሰናል መካከል ይከናወናል፡፡

ቶተነሃም ሆትስፐርም ከ ሳውዛምፕተን ጋር ይፋለማል፡፡

ሊጉን ማንችስተር ሲቲ በ38 ነጥቦች ሲመራ ሊቨርፑል በ36 ነጥብ 2ኛ፤ ቼልሲ በ31 ነጥብ 3ኛ፣ አርሰናልና ቶተንሃም ደግሞ በእኩል 30 ነጥቦች በግብ ክፍያ ተበላልጠው 4ኛ እና 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *