loading
የ13ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የማጠቃለያ ፕሮግራም ትናንት ተካሄደ

የ13ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የማጠቃለያ ፕሮግራም ትናንት ተካሄደ

ፌዴሬሽኑ በከተማው ተቀማጭነታቸውን ካደረጉ በሁሉም የሊግ እርከኖች ተሳታፊ ከሆኑ ክለቦች ጋር በኢንተርኮንትኔንታል አዲስ ሆቴል ውይይት አካሂዷል፡፡

በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የከተማው የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለሰማዕት መርሐጥበብን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኃይለየሱስ ፍሰሀ (ኢንጂነር) በተገኙበት ተካሂዷል።

ለውይይት ከቀረቡት መነሻ ሀሳቦች መካከል ፌዴሬሽኑ ለክለቦች ስለሚያደርገው ድጋፍ፣ የማዘውተሪያ ቦታዎች ችግር እና የስፓርታዊ ጨዋነት ጉዳዮች ዋንኞቹ ነበሩ፡፡ በተጨማሪም ከከተማው ትልቅነት አንጻር ፌደሬሽኑ ከሲቲ ካፕ ውድድር በዘለለ ሌሎች የገቢ መፍጠሪያ እድሎችን በመፍጠርና በመጠቀም ደረጃ ሰፊ ክፍተቶች እንዳሉበት በተሳታፊዎች ተነስቷል፡፡

አቶ ኃይለሰማዕት በምላሻቸው የማዘውተሪያ ችግሮችን ለመፍታት በከተማው በሚገኙ 117 ወረዳዎች በተለዩ ክፍት ቦታዎች ላይ 117 መለስተኛ የእግር ኳስ ሜዳዎች ለመስራት ቦታዎች መለየታቸውን፤  በተጨማሪም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማኅበር በአሁኑ ወቅት በእጁ የሚገኘውን ሜዳ የእግርኳስ ቡድኑን መልሶ የማያቋቋም ከሆነ ስለመንጠቅም እየታሰበ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የከተማዋ ክለቦች ህዝባዊ መሠረት እንዲኖራቸው መስራቱ የተሻለው አማራጭ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዕለቱ በ13ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ውድድር ተሳታፊዎች የሽልማት እንዲሁም የእውቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡ ከውድድሩ ከተገኘው 1.81 ሚልየን ብር ጠቅላላ ገቢም ፌደሪሽኑ ከወጪ ቀሪ 1.3 ሚልየን ብር በውድድሩ ተሳታፊ ለነበሩ 8 ክለቦች በሽልማት መልክ ተበርክቷል፡፡

በዚህም ለውድድሩ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ማኅበራት፣ ተቋማት እና ግለሰቦች የምስክር ወረቀትና ሽልማት ተበርቷል፡፡

ፋሲል ከነማ፣ ወላይታ ድቻ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ አዳማ ከተማ ለተሳታፊነታቸው 81ሺህ 76 ብር ሽልማት ሲበረከትላቸው፤ ውድድሩን በአራተኛ ደረጃ ያጠናቀቀው መከላከያ የ108,101.78 ፤ በሶስተኛ ደረጃ ያጠናቀቀው ጅማ አባጅፋር የ189,178.12፤ በቅደም ተከተል አንደኛና ሁለተኛ ሆነው ያጠናቀቁት ኢትዮጵያ ቡናና ባህር ዳር ከነማ 405,381.68 እና 270,254.46 ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በተጨማሪም ለውድድሩ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ማኅበር የ100 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የአዲስአበባ እግርኳስ ፌደሪሽን ለከተማው እግርኳስ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ያላቸውን 5 ግለሰቦችን የእውቅና ሽልማት አበርክቷል፡-

  1. ኢንስትራክተር ሽፈራው እሸቱ
  2. ኑራ ኢማም
  3. አሰልጣኝ ሰኢድ
  4. አሰልጣኝ ግዛው
  5. አቶ ጌታቸው አበበ

ሶከር ኢትዮጵያ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *